fredag 11 december 2015

“መሬት ለአራሹ” ተረስቶ “መሬት ለካድሬ” – ከአምዶም ገብረሥላሴ


oromo
“መሬት ለኣራሹ” የሚል 60ዎቹ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች መፎክር ነበር።
የጃንሆይ ዙፋን መገርሰስ ዋነኛ ምክንያት ሆነ። ደርግም ጥያቄው ህዝቡ በሚፈልገው መልኩ ኣልመለሰውም።
ህወሓት ደርግ ገርስሶ 4 ኪሎ ከገባ በኋላም የመሬት ጥያቄ “መሬት የህዝብና መንግስት ናት። መንግስት ማለት ህዝብ ሰለ ሆነ እኔ ራሴ የመሬት ባለቤት ነኝ” ብሎ በማወጅ ህዝባችን መሬት ኣልባ ኣደረገው።
“መሬት ለኣራሹ” ትቶ መሬት ለካድሬ የሚል ውስጣዊ መፎክር ለ25 ዓመታት ተግባራዊ ኣድርገዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘ እስቲ ሰሞኑ በውቕሮ የተጋለጠ ጉድ እንደምሳሌ ላቅርብ።
የውቕር ከተማ ከንቲባ ኣቶ ዘርኡ ገብረመስቀል እያሉ ኣቶ ገብረዝሄር ገብረመድህን የተባሉ ባለ ሃብት “ማድያ ለመክፈት ስለምፈልግ በኣውራ ጎዳና መስመር መሬት ይሰጠኝ” ኣሉ።
ማድያ እንዲሰሩበት የመረጡት መሬት 1200ካ/ሜ ሲሆን በውቕሮ ከተማ ገበያ ለካሬ ሜትር 700 ብር በሊዝ ገበያ የተወሰነለት ነው።
ባለሃብት በሊዝ ዋጋ ከገዛው 840 000 ብር መክፈል ነበራቸው ይሁን እንጂ ይሄ ብር ከመክፈል ከውቕሮ ከንቲባ ኣቶ ዘርኡ ገብረመስቀል ጋራ ተደራደሩ በድርድራቸውም ስምምነት ላይ ደረሱ። ከከንቲባው ጋር 4 ሰዎች ከባለ ሃብቱ ተደራደሩ።
oromo2
በድርድሩ ወደ መንግስት ካዝና ሊገባ የነበረውና በባለሃብቱ ሊከፈል የታሰበው 840 000 ብር ግማሹ እንዲቀርና ግማሹም ለኣምስት ሰዎች እንዲካፈሉት ወሰኑ። በዚህ መሰረት
1) ኣቶ ዘርኡ ገብረመስቀል 250 000 ብር
2) ምክትል ከንቲባ ገብረመድህን ስዩም 70 000
3) ተኽለ ኣብርሃ የመሬት ማልማት ፅፈት ቤት ሓላፊ( መዛገጃቤት) 50 000 ብር
4) ጊደና በርሀ የውቅሮ መሃንዲስ 50 000 ብር ተካፈሉት።
በዚህ መሰረት ኣቶ ገብረዝሄር ገብረመስቀል ሊከፍሉት ከነበረው ዋጋ በግማሽ ቀንሰው ለካሬ ሜትር በ23 ብር 420 000 ብር ለባለስልጣናት በመክፈል ከግማሽ በላይ ቅናሽ ኣግኝተዋል።
ሰሞኑ በትግራይ የህወሓት ካብኔ ኣባላት ግምገማዎች እያካሄዱ ይገኛሉ። በስብሰባው የተለያዩ ኔትወርኮች ያሉት ሲሆኑ ራስ በራስ እየተጠላለፉ ይገኛሉ።
በውቕሮ ከተማ እየተካሄደ ያለው ግምገማ የካቢኔ ባለስልጣናት ይሄ ሙስና ኣጋለጡ። በዚህ መሰረትም ከንቲባው ኣቶ ርኡ፣ የማዘጋጃቤት መሬት ማልማት ሓላፊ ተኽለ ፣ የውቕሮ ከተማ መሓንዲስ ጊደና በርሀ ሲታሰሩ ምክትል ከንቲባ ገብረመድህን ስዩም 70 000 ብር ሙሰኛ ባልታወቀ ምክንያት ኣልታሰረም።
መሬቱ ከኣራሹ ተቀምቶ ለካድሬው ጥቅም እየዋለ ይገኛል።
ኣቶ ሓየሎም በላይ 1200 ካ/ሜ መሬታቸው በከንቲባና ባለ ሃብቱ ያለ ካሳ ክፍያና የመሬት ልዋጭ ተነጥቀዋል። ኣብየቱታቸው እስከ ዞን ድረስ ቢያሰሙም ምንም መፍትሄ ኣልተሰጣቸውም።
tigrai
በተያያዘ ዜና የመቐለ ከንቲባ ነበርና የማእከላዊ ኮሚቴ ኣባል የነበሩ ጉምቱ ባለ ስልጣንም ደብሪ በተባለ የገጠር ቀበሌ በሚስታቸው ስም ከኣንድ ገበሬ መሬት ቀምተው ኣርሶ ኣደሩ መሬት ኣልባ ሲያደርጉት ከቀበሌ እስከ ክልል ኣብየት ቢል ሰሚ እንዳላገኘ በሓድነት ክፍለ ከተማ በህዝብ ግምገማ ተጋልጠዋል።
የኣይናለም፣ እግሪሓሪባ ወዘተ ገበሬዎች በካድሬዎችና ባለስልጣናት ያለኣግባብ መሬታቸው እመተቀሙ መሬት ኣልባ ሁነዋል።
እንደነ ወይዘሮ ኣልጋነሽ ገብሩ የመሳሰሉ ጀግኖች ደግሞ መሬታችን ኣሳልፈን ኣንሰጥም በማለታቸው ለእስር ተዳርገው ይገኛሉ።
ይሄው ኣርሶ ኣደሩ ባገሩ መሬት ኣልባ ሲሆን ካድሬው ግን ከገበሬው እየቀማ ባለሃብት እየሆነ ነው።
የኦርሞ ህዝብ “የኣዲስ ኣበባ ማስፋፍያ ማስተር ፕላን ገበሬው መሬት ኣልባ ያደርግብናል” በማለት እየተቃወመው ይገኛል። ይሄ ተቃውሞ ከ25 ዓመታት የኢህኣዴግ ኣገዛዝ ልምድ ተነስተን መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሊደግፈው ይገባል።
መንግስትም ህዝቡ ያልተቀበለው እቅድ በመሰረዝና ሰልፉ ለመበተን የተጠቀመው ያልተመጣጠነ የሃይል እርምጃና ላደረሰው ጉዳት በድፍረት ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባዋል።
ኢህኣዴግ የመሬት ፖሊሲዎቹ መቀየር ኣለበት። መንግስት የኦሮሞ ህዝብ ሰለማዊ ተቃውሞ በኣግባቡ መመለስ ብቻ ሳይሆን ከመሬት ባለቤትነቱም መራቅና የማስተዳደር ስራ ብቻ እንዲታቀብ እንመክረዋለን።
ህወሓትና የትግራይ ህዝብ መለየት ያቃታቹ የህወሓት ካድሬዎችና ፅንፈኛ በጥላቻ ዓይናቹ የታወረው ተቃዋሚዎች ኣትድከሙ።
የትግራይ ህዝብ ከኦሮሞና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ጎን በኣንድነት ተሰልፎ ለውጥ እውን ያደርጋል። ህዝባችን በተግባር የሚደግፈው ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንጂ በስሙ የሚነግድለት ኣምባገነን ስርዓት ኣያስፈልገውም።
ነፃነታችን በእጃችን ነው።

Inga kommentarer:

Skicka en kommentar