(ዘ-ሐበሻ) በምዕራብ አሪሲ አዳባ ከተማ ለሰላማዊ ሰልፍ በወጡ የህብረተሰቡ ክፍል ላይ የአጋዚ ጦር ወታደራዊ እርምጃ መውሰዱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ:: በከተማዋ የአጋዚ ጦር በወሰደው እርምጃ የጥይት ድምጽ እና ጭስ ከተማዋን ሞልቶት እንደዋለ ነዋሪዎቹ አስታውቀዋል::
እንደ ነዋሪዎች ገለጻ ከሆነ በአዳባ ከተማ በአጋዚ ጦር በተወሰደው ወታደራዊ እርምጃ አንድ ወጣት ተገድሏል:: በአዳባ የተገደለው ወጣት ስም ነስረዲን መሀመድ እንደሚባልም ታውቋል::
በአሁኑ ሰዓት ወደ አዳባ ከተማ መግባትም ሆነ መውጣትም የማይቻል ሲሆን ወታደሮች ከተማዋን አጥረዋታል:: በአጋዚ ጦር ጥቃት የቆሰሉት ወገኖች በሃዋሳ እና ኩረያ ሆስፒታል እያታከሙ መሆኑም ተሰምቷል::
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/48998#sthash.gn7pTMza.dpuf
Inga kommentarer:
Skicka en kommentar