onsdag 16 december 2015

የቀድሞው ጠ/ሚ/ር ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን የሰሞኑ ሕዝባዊ ቁጣ ለቤተሰቧና ለንብረቷ እንድታስብ እንዳደረጋት ገለጸች

የቀድሞው ጠ/ሚ/ር ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን የሰሞኑ ሕዝባዊ ቁጣ ለቤተሰቧና ለንብረቷ እንድታስብ እንዳደረጋት ገለጸች 



azeb
(ዘ-ሐበሻ) በአንድ ወቅት “ደሃ ነኝ… ከዓለማችን የደሃ ሀገር መሪዎች መካከል እኛ አንደኞቹ ነን” ስትል የነበረችው የቀድሞው ሟች ጠቅላይ ሚ/ር መለስ ዜናዊ ባለቤት ወይዘሮ አዜብ መስፍን ሰሞኑን በኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች የተቀጣጠለውን ሕዝባዊ አመጽ ተከትሎ በገንዘቧና በቤተሰቧ ላይ ያሳደረውን ስጋቷን በፌስቡክ ገጿ ገለጸች::
Screen Shot 2015-12-16 at 3.54.28 AM
ወ/ሮዋ በፌስቡክ ገጿ እንዳለችው “በሰሞኑ በሚሆነው ነገር በጣም በጣም የሚያሳዝን ነው። እኛ እንግዲህ አስራ ሰባት አመት ትግል ቦኅላ ለዚህ ድል በቅተን ደርግን ገርስሰን ለመላው ኢትዮጵያዊ ዲሞክራሲ ያለባት አገር መስርተናል። እና መለስ ልጅነቱን በሙሉ የለፋበትን አላማ ዛሬ በዚህ ብጥብጥ ባነሱ አደገኛ ቦዘኔዎች ከልማት ታቅበን መቀመጥ በጣም ያሳዝናል በእውነቱ። ስራ አቁሞ ሰልፍ ሲሰለፉ መዋል ምን ይባላል? ብንሰራ አይሻልም? እንደ የድሮ ስርአት ነፍጠኞች ያሁኑ አገር ባይበጠብጡ ይሻላል።”
ወ/ሮዋ አክላም ” ትልልቅ አዋቂ ሰዎች የመለስ አይምሮ ያፈለቀውን ራእይ የሚያስፈፅሙ አሉ ተመርጠው በህዝብ መቶ ድምፅ ተሰጥቷቸ እያሉ አሁን ለምን አገር ይረበሻል? እኔ በእውነቱ ከሆነ ለቤተሰብ ለንብረቴ ማሰብ ጀምሬያለሁ። እርግጠኛ ነኝ ብዙዎች እንደኔው ማሰብ መስጋት ጀምረዋል። ጥሩ አይደለም ሰላም እና መረጋጋት ያስፈልጋል በመጀመሪያ።” ብላለች::
ስለ ባሏ ራዕይ ከሞተ በኋላም እንዲነገር የምትፈልገው ወይዘሮ አዜብ ሕዝብ የመለስን ፓርክ በማቃጠሉ የተሰማትን ስሜት ስትገልጽም “የመለስ እሚያህል ትልቅ ሰው በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ እማይታወቅ ሰው፣ ከዚህ በፊትም እንዳልኩት በፔሮል የሚተዳደር ፕሬዚደንት በሶስት ሺህ ብር ደሞዝ የትም አለም የለም። እና ዛሬ ለመታሰቢያ አንድ ፓርክ ቢሰራ እነዚ ሰልፍ ወጡ የተባሉ አደገኛ ቦዘኔዎች አቃጠሉ አሉ። ሀዘኔ መሪር ነው በእውንት ከሆነ። መለስ ቢያየን ያፍርብናል። ራእይ ሰጥቶን ያ ሁሉ አይምሮ ጨምቆ አውጥቶ እኛ እንዲ ወደ ድንቁርና ስንሄድ ያሳዝነዋል። በቶሎ መንግስ ፀጥታ ሊያስከብር ይገባዋል። እነዚ ቦዘኔዎችም ለፍርድ መቅረብ አለባቸው።” ብላለች::
የቀድሞው ጠ/ሚ/ር ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን የሰሞኑ ሕዝባዊ ቁጣ ለቤተሰቧና ለንብረቷ እንድታስብ ካደረጋት ቀጣይ እቅዷ ገንዘቧን አሽሽታ ወደ ሌላ ሃገር መፈርጠጥ? ይህ የሕዝብ ጥያቄ ነው::

fredag 11 december 2015

“መሬት ለአራሹ” ተረስቶ “መሬት ለካድሬ” – ከአምዶም ገብረሥላሴ


oromo
“መሬት ለኣራሹ” የሚል 60ዎቹ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች መፎክር ነበር።
የጃንሆይ ዙፋን መገርሰስ ዋነኛ ምክንያት ሆነ። ደርግም ጥያቄው ህዝቡ በሚፈልገው መልኩ ኣልመለሰውም።
ህወሓት ደርግ ገርስሶ 4 ኪሎ ከገባ በኋላም የመሬት ጥያቄ “መሬት የህዝብና መንግስት ናት። መንግስት ማለት ህዝብ ሰለ ሆነ እኔ ራሴ የመሬት ባለቤት ነኝ” ብሎ በማወጅ ህዝባችን መሬት ኣልባ ኣደረገው።
“መሬት ለኣራሹ” ትቶ መሬት ለካድሬ የሚል ውስጣዊ መፎክር ለ25 ዓመታት ተግባራዊ ኣድርገዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘ እስቲ ሰሞኑ በውቕሮ የተጋለጠ ጉድ እንደምሳሌ ላቅርብ።
የውቕር ከተማ ከንቲባ ኣቶ ዘርኡ ገብረመስቀል እያሉ ኣቶ ገብረዝሄር ገብረመድህን የተባሉ ባለ ሃብት “ማድያ ለመክፈት ስለምፈልግ በኣውራ ጎዳና መስመር መሬት ይሰጠኝ” ኣሉ።
ማድያ እንዲሰሩበት የመረጡት መሬት 1200ካ/ሜ ሲሆን በውቕሮ ከተማ ገበያ ለካሬ ሜትር 700 ብር በሊዝ ገበያ የተወሰነለት ነው።
ባለሃብት በሊዝ ዋጋ ከገዛው 840 000 ብር መክፈል ነበራቸው ይሁን እንጂ ይሄ ብር ከመክፈል ከውቕሮ ከንቲባ ኣቶ ዘርኡ ገብረመስቀል ጋራ ተደራደሩ በድርድራቸውም ስምምነት ላይ ደረሱ። ከከንቲባው ጋር 4 ሰዎች ከባለ ሃብቱ ተደራደሩ።
oromo2
በድርድሩ ወደ መንግስት ካዝና ሊገባ የነበረውና በባለሃብቱ ሊከፈል የታሰበው 840 000 ብር ግማሹ እንዲቀርና ግማሹም ለኣምስት ሰዎች እንዲካፈሉት ወሰኑ። በዚህ መሰረት
1) ኣቶ ዘርኡ ገብረመስቀል 250 000 ብር
2) ምክትል ከንቲባ ገብረመድህን ስዩም 70 000
3) ተኽለ ኣብርሃ የመሬት ማልማት ፅፈት ቤት ሓላፊ( መዛገጃቤት) 50 000 ብር
4) ጊደና በርሀ የውቅሮ መሃንዲስ 50 000 ብር ተካፈሉት።
በዚህ መሰረት ኣቶ ገብረዝሄር ገብረመስቀል ሊከፍሉት ከነበረው ዋጋ በግማሽ ቀንሰው ለካሬ ሜትር በ23 ብር 420 000 ብር ለባለስልጣናት በመክፈል ከግማሽ በላይ ቅናሽ ኣግኝተዋል።
ሰሞኑ በትግራይ የህወሓት ካብኔ ኣባላት ግምገማዎች እያካሄዱ ይገኛሉ። በስብሰባው የተለያዩ ኔትወርኮች ያሉት ሲሆኑ ራስ በራስ እየተጠላለፉ ይገኛሉ።
በውቕሮ ከተማ እየተካሄደ ያለው ግምገማ የካቢኔ ባለስልጣናት ይሄ ሙስና ኣጋለጡ። በዚህ መሰረትም ከንቲባው ኣቶ ርኡ፣ የማዘጋጃቤት መሬት ማልማት ሓላፊ ተኽለ ፣ የውቕሮ ከተማ መሓንዲስ ጊደና በርሀ ሲታሰሩ ምክትል ከንቲባ ገብረመድህን ስዩም 70 000 ብር ሙሰኛ ባልታወቀ ምክንያት ኣልታሰረም።
መሬቱ ከኣራሹ ተቀምቶ ለካድሬው ጥቅም እየዋለ ይገኛል።
ኣቶ ሓየሎም በላይ 1200 ካ/ሜ መሬታቸው በከንቲባና ባለ ሃብቱ ያለ ካሳ ክፍያና የመሬት ልዋጭ ተነጥቀዋል። ኣብየቱታቸው እስከ ዞን ድረስ ቢያሰሙም ምንም መፍትሄ ኣልተሰጣቸውም።
tigrai
በተያያዘ ዜና የመቐለ ከንቲባ ነበርና የማእከላዊ ኮሚቴ ኣባል የነበሩ ጉምቱ ባለ ስልጣንም ደብሪ በተባለ የገጠር ቀበሌ በሚስታቸው ስም ከኣንድ ገበሬ መሬት ቀምተው ኣርሶ ኣደሩ መሬት ኣልባ ሲያደርጉት ከቀበሌ እስከ ክልል ኣብየት ቢል ሰሚ እንዳላገኘ በሓድነት ክፍለ ከተማ በህዝብ ግምገማ ተጋልጠዋል።
የኣይናለም፣ እግሪሓሪባ ወዘተ ገበሬዎች በካድሬዎችና ባለስልጣናት ያለኣግባብ መሬታቸው እመተቀሙ መሬት ኣልባ ሁነዋል።
እንደነ ወይዘሮ ኣልጋነሽ ገብሩ የመሳሰሉ ጀግኖች ደግሞ መሬታችን ኣሳልፈን ኣንሰጥም በማለታቸው ለእስር ተዳርገው ይገኛሉ።
ይሄው ኣርሶ ኣደሩ ባገሩ መሬት ኣልባ ሲሆን ካድሬው ግን ከገበሬው እየቀማ ባለሃብት እየሆነ ነው።
የኦርሞ ህዝብ “የኣዲስ ኣበባ ማስፋፍያ ማስተር ፕላን ገበሬው መሬት ኣልባ ያደርግብናል” በማለት እየተቃወመው ይገኛል። ይሄ ተቃውሞ ከ25 ዓመታት የኢህኣዴግ ኣገዛዝ ልምድ ተነስተን መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሊደግፈው ይገባል።
መንግስትም ህዝቡ ያልተቀበለው እቅድ በመሰረዝና ሰልፉ ለመበተን የተጠቀመው ያልተመጣጠነ የሃይል እርምጃና ላደረሰው ጉዳት በድፍረት ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባዋል።
ኢህኣዴግ የመሬት ፖሊሲዎቹ መቀየር ኣለበት። መንግስት የኦሮሞ ህዝብ ሰለማዊ ተቃውሞ በኣግባቡ መመለስ ብቻ ሳይሆን ከመሬት ባለቤትነቱም መራቅና የማስተዳደር ስራ ብቻ እንዲታቀብ እንመክረዋለን።
ህወሓትና የትግራይ ህዝብ መለየት ያቃታቹ የህወሓት ካድሬዎችና ፅንፈኛ በጥላቻ ዓይናቹ የታወረው ተቃዋሚዎች ኣትድከሙ።
የትግራይ ህዝብ ከኦሮሞና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ጎን በኣንድነት ተሰልፎ ለውጥ እውን ያደርጋል። ህዝባችን በተግባር የሚደግፈው ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንጂ በስሙ የሚነግድለት ኣምባገነን ስርዓት ኣያስፈልገውም።
ነፃነታችን በእጃችን ነው።

የአጋዚ ሰራዊት በምዕራብ አሪሲ አዳባ ከተማ ወታደራዊ ጥቃት ፈጸመ – አንድ ወጣት መገደሉ ተሰማ

adaba
(ዘ-ሐበሻ) በምዕራብ አሪሲ አዳባ ከተማ ለሰላማዊ ሰልፍ በወጡ የህብረተሰቡ ክፍል ላይ የአጋዚ ጦር ወታደራዊ እርምጃ መውሰዱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ:: በከተማዋ የአጋዚ ጦር በወሰደው እርምጃ የጥይት ድምጽ እና ጭስ ከተማዋን ሞልቶት እንደዋለ ነዋሪዎቹ አስታውቀዋል::
እንደ ነዋሪዎች ገለጻ ከሆነ በአዳባ ከተማ በአጋዚ ጦር በተወሰደው ወታደራዊ እርምጃ አንድ ወጣት ተገድሏል:: በአዳባ የተገደለው ወጣት ስም ነስረዲን መሀመድ እንደሚባልም ታውቋል::
በአሁኑ ሰዓት ወደ አዳባ ከተማ መግባትም ሆነ መውጣትም የማይቻል ሲሆን ወታደሮች ከተማዋን አጥረዋታል:: በአጋዚ ጦር ጥቃት የቆሰሉት ወገኖች በሃዋሳ እና ኩረያ ሆስፒታል እያታከሙ መሆኑም ተሰምቷል::
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/48998#sthash.gn7pTMza.dpuf

በኦሮሚያ ዛሬ ብቻ የተገደሉት ወጣቶች ቁጥር 5 ደረሰ


oromo brother
(ዘ-ሐበሻ) ሁለተኛ ሳምንቱን የያዘውና በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ከተሞች እየተደረገ ያለው ከባድ ተቃውሞ እንደቀጠለ ባለበት በዚህ ሰዓት በአጋዚ ጦር ዛሬ ብቻ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ወደ 5 ማደጉ ተገለጸ::
oromo
ከተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች እየመጡ ያሉት መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ በፌደራልና አጋዚ ጦር በኢናንጎ ከተማ 3; በባኮ ከተማ 1 እንዲሁም በባቢቺ ከተማ 1  ወጣት (የሟቾች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊያድግ ይችላል) ተገድለዋል::

ለዘ-ሐበሻ በደረሰው መረጃ በአምቦ ሆስፒታል በቁስለኞች ተጥለቅልቋል::
በአጋዚ ጦር ተጎድተው በአምቦ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ከሚገኙት መካከል
1ኛ ታመን ውቤ ደምሰው
2ኛ ዓለሙ ለማ
3ኛ. ፍጹም አየለ
4ኛ. ሽመልስ ዘሪሁን
5ኛ ማሙሽ ሃያሉ
6ኛ ገመቹ ሃሬርሳ
7ኛ ሚሚ ቶሎሳ እንደሚገኙበት ታውቋል::
እንደዚሁም በጅማ ሆስፒታል ቁሰለኞችን ሲያክሙ የቆዩ የህክምና ባለሙያዎች ሳይቀሩ ተቃውሟቸውን ማሰማት ጀምረዋል::
በሌላ ዜና የአዲስ አበባ እና የጂማ መንገድ መዘጋቱን የሚገልጹት ዘገባዎች በዲላ ከተማም እንዲሁ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ እየተደረገ ነው ብለዋል:: በተቃውሞው የተነሳ መንገዱ በመዘጋቱ መኪኖች በጠቅላላ ቱሉቦሎ ላይ ቆመዋል::
በኦሮሚያ ክልል የተነሳውን የሕዝብ ቁጣ ለማብረድ የፌደራል ፖሊስ እና የአጋዚ ጦር በየአካባቢው ያሉ የነዋሪዎችን ጭነት መኪናዎች አስገድደው በመውሰድ ሰራዊት በመጫን ሕዝብ ለመጉዳት እየተጠቁመበት እንደምገኙ የአይን እማኞች ይናገራሉ::
ዘ-ሐበሻ በኦሮሚያ ክልል የተነሳውን የሕዝብ ቁጣ እየተከታተለች መዘገቧን ትቀጥላለች::
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/48927#sthash.XVWvJODD.dpuf

በሚኒሶታ ፍቅር ያሸነፈበት ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተደረገ



(ዘ-ሐበሻ) በሚኒሶታ የሚገኘው የኦሮሞ ማህበረሰብ ነበር በቅድሚያ ይህን የኦሮሞ ተማሪዎችን ጥያቄ ለመደገፍ ሰላማዊ ሰልፍ የጠራው:: ይህን ተከትሎ በሚኒሶታ የሚገኘው የኢትዮጵያ ወጣቶች ንቅናቄ ሰልፉን እንደሚቀላቀልና ሰላማዊ ሰልፉን ደግፉ ከኦሮሞ ወንድም እና እህቶቹ ጋር እንደሚቆም መግለጫ አወጣ::
Ethiopia Minnesotaethiopia minnesota 3ethiopia Minnesota2
ይህ ሰልፍ በሰፊው ሚኒሶታ የአንድነት ምላሽ ማግኘቱን የተረዱና በኦሮሞ ሕዝብ ስም የሚነግዱ የሕወሓት መንግስት ተላላኪዎች ኢትዮጵያዊያኑን “በዚህ ሰልፍ ላይ የኢትዮጵያ ባንዲራም ሆነ ሌላ መል ዕክት ይዛችሁ መገኘት የለባችሁም.. ይህን ካደረጋችሁ ብጥብጥ ሊፈጠር ይችላል” የሚል ቅስቀሳ ማድረግ ጀመሩ:: ሆኖም እንዲህ ያለው ሕዝብ ሲገደል በአንድነት መቆም ሲገባ የሚያራርቅ ሥራ የሚሰሩት በኦሮሞ ሕዝብ ስም የሚነግዱ የሕወሓት መንግስት ተላላኪዎች መሆኑን የተረዱት ወገኖች ሰልፉን የኢትዮጵያን ባንዲራ ይዘው; የተላላኪዎቹን ማስፈራሪያ ወደጎን ትተው ጥያቄያችሁ ጥያቄያችን ነው በሚል ተቀላቅለውታል:: የሕወሓት መንግስት ተሸነፈ!!! ያሰበው ተንኮልና ሕዝብን ከሕዝብ የማራራቅ ተግባር በፍቅር ተሸንፏል::
ዛሬ በሚኒሶታ ስቴት ካፒቶል ደጃፍ ላይ ከቀኑ በ12 ሰዓት ነበር ይህ ሰላማዊ ሰልፍ የተጠራው:: ሰልፉ በተጠራበት ሰዓት ዝናብ እየዘነበ ነበር:: ባሃገር ቤት ሕዝብ ላይ የሕወሓት መንግስጥ ጥይት እያወረደ እኛ ዝናብ ቢወርድብን ልንፈራ ነው ወይ? ያሉ የሰልፉ ታዳሚዎች ስቴት ካፒቶሉን አጥለቀለቁት::
በሰልፉ ላይ የኦሮሞ ማህበረሰብ; የኦጋዴን ማህበረሰብ እና የእናትየው የኢትዮጵያ ባንዲራም ተውለብልቧል:: ለሕወሓት መንግስት በኦሮሚያ ምድር ላይ ንጹሃንን መገደሉን እንዲያቆም; በልማት ስም ገበሬዎችን ራቁቱን እያስቀረ መሬት መቸብቸቡን እንዲያቆም; ብሎም ያን ምድር ለቆ እንዲወጣ ተጠይቋል:: የአሜሪካ መንግስትም ከሕወሓት መንግስት ጋር እንዳይተባበር ሕዝቡ አምርሮ ጠይቋል::
Minnesota ethiopia
ሰልፉ እየተደረገ ባለበት ወቅትም ወንድማማች የሆኑ ሕዝቦች በአንድ ላይ የተለያዩትን ባንዲራዎች በአንድ ላይ በመያዝ ለመጀምሪያ ጊዜ የአንድነት ፍቅር የተሞላበት ፎቶግራፎችን ሲነሱ ነበር:: በሚኒሶታ እንዲህ ያለውን ፍቅር እና አንድነት ለመመስረት ከፍተኛ የሆነ መስዋዕትነት እየተከፈለ ባለበት ሰዓት የሕወሃት መንግስት ተላላኪ የሆኑ ወገኖች በኦሮሞ ሕዝብ ስም ከኦሮሞ ሕዝብ ጎን እንቆማለን የሚሉትን ስም እየሰጡ የማንጓጠጥ ሥራ መስራታቸውን የማቆሚያ ጊዜው አሁን እንደሆነ ይህ ሰልፍ አሳይቶናል::
ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያውያን በሊቢያ ሲገደሉ አዝኖ እዚሁ ዛሬ ሰልፍ የተደረገበት ቦታ ላይ የወጡ ሁሉ ዛሬም እዚሁ ነበሩ:: በሞቱት ወገኖች ብናዝንም አንድነትና ፍቅራችንን በመመለሱ ደግሞ እንኮራለን::
በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ከሰልፈኞቹ እንደተነገረው የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ መብቱ እንዲከበርለት መጠየቅ እንጂ ከየትኛውም ብሄር ብሄረሰብ ጋር ለመጋጨት አይደለም:: አንዱን ከሌላው ለይቶ ከዚያ መሬት እንዲሰናበት መጠየቅ አይደለም::

የአ. አበባን ማስተር ፕላንን በመቃወምና ለተገደሉት ተማሪዎች አጋር ለመሆን በአውስትራሊያ ቪክቶሪያ የተደረገ ሰላማዊ ሰልፍ - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/48979#sthash.v5k3VlsE.dpuf


በቪክቶሪያ የኦሮሞ ማኅበረሰብ ማኅበር አባላት፤ የአዲስ አበባን ማስተር ፕላንን በመቃወምና ኦሮሚያ ክልል ውስጥ በተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች ሳቢያ ህይወታቸውን ላጡት ወጣቶች ድጋፋቸውን በመቸር ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል። የተቃውሞና የድጋፍ ሰልፉ የተካሄደውም ዓርብ፤ ዲሴምበር 11 2015 ሜልበርን ከተማ ውስጥ ነው።

የአ. አበባን ማስተር ፕላንን በመቃወምና ለተገደሉትን ተማሪዎች አጋር ለመሆን በአውስትራሊያ ቪክቶሪያ የተደረገ ሰላማዊ ሰልፍ | Audio

በአንዋር መስጊድ የፈነዳው ምንነቱ ያልታወቀውን ፈንጂን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ


  • 320
     
    Share
anwarከቢቢኤን ራድዮ የተገኘው ተጨማሪ መረጃ እንደሚያመለክተው በዛሬው ዕለት በታላቁ አንዋር መስጊድ የፈነዳው ያልታወቀ ፈንጂን ደህንነቶች የ ኤሌክትሪክ ፍንዳታ ነዉ የሚል የተሳሳተ መረጃ እያሰራጩ ነዉ ሲሉ እማኞች ገልጸዉልናል ብሏል:። ራድዮው ምንጮቼ ገለጹልኝ እንዳለ መዉሊድን አስመልክቶ ይበተን ከነበረ ከረሜላ ጋር አብሮ በሶፍት ወረቀት የተጠቀለለ ነገር ሰዎች ላይ ወድቆ ነዉ ፍንዳታዉ የተከሰተዉ።
ራድዮው እንደዘገበው ከሰዉነት ላይ የተቆረጠ ስጋ የፈሰሰ ደም ያለበት ፎቶ ግራፍ በሶሻል ሚድያዎች የተለቀቀ ሲሆን ፍንዳታዉ እንደተከሰተ ደህንንነቶች ግቢዉን የመቆጣጠራና የማጽዳት ስራ ላይ ነበሩ። ግቢዉ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዉሉ ከተጠረገ በሗላ ከጠረጋ የተረፈ የሰው ስጋ (ሙዳ ስጋ)አግኝተዉ ፎቶ ማንሳታቸዉን እማኞቻችን ነግረዉናል ሲል ራድዮው ዘገቧል::
በዚህ ምንነቱ ያልታወቀና ከወደላይ ተወርውሮ የመጣ ነው በተባለው ፈንጂ የተነሳ 6 ሰዎች ቆስለው ተክለሃይማኖት ሆስፒታል ህክምና ላይ ናቸው::
1 የሞተ ሰውም አለ እየተባለ ሲሆን ዘ-ሐበሻ ይህን ለማጣራት እየሞከረች ነው::
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/48988#sthash.VjwMozQg.dpuf

torsdag 5 november 2015

በቡሬ ግንባር ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የህወሓት መራሹ መከላከያ ሰራዊት አባላት ከዱ



clash
(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ) ባጠቃላይ በአራቱም ማዕዘን የኢትዮጵያ ጠረፎች በቀበሮ ጉድጓድ ውስጥ የሚኖረው በህወሓት ቁጥጥር ስር የሚገኘው መከላከያ ሰራዊት አባላት በየዕለቱ ያለማቋረጥ ስርዓቱን እየከዱ ሲሆን በተለይም ደግሞ ከሰሞኑ ቡሬ ግንባር በስልጠና ላይ ይገኙ የነበሩ እጅግ በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወታደሮች ያገኙትን ቀዳዳ ተጠቅመው በቡድን በቡድን እየሆኑ በመሽሎክ ከአካባቢው ተሰውረዋል፡፡ ወሎ ውስጥ ከአንድ ቀበሌ ብቻ 10 ወታደሮች ከጦር ግንባር ከድተው ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡

አሁንም ቢሆን አብዛኛው ሰራዊት መሽሎኪያ ቀዳዳ እያነፈነፈ ሊከዳ በቋፍ ላይ እንደሚገኝ የመከላከያ ምንጮቻችን የላኩት መረጃ ያረጋግጣል፡፡

- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47951#sthash.oKSR1DMe.dpuf

ሰማያዊ ፓርቲ መግለጫ አወጣ – “ከነካባው የተቀበረውን የፍትህ ሥርዓት ነፃ ለማውጣት ትግላችን አጠናክረን እንቀጥላለን!”

(ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ)

ኢትዮጵያ ውስጥ ከህገ መንግስቱ ጀምሮ አዋጅና በሌሎችም የዜጎችን መብት የሚደነግጉ በርካታ መሰረቶች ቢኖሩም ለይስሙላ ህጋዊ ሥርዓት እንዳለ ከማስመሰልም አልፎ ለአገዛዙ ማጥቂያና መግዢያ ከመሆን ባለፈ የዜጎችን መብት እያስከበሩ አይደለም፡፡ ባለፉት 6 ወራት እንኳን ህግ እንደተቀበረች፣ በዚሁ አገዛዙ ውስጥ ተፅዕኖ ያለው የፍርድ ቤት አልፎ አልፎ የሚወስነው ውሳኔ በፖሊስ ቀጭን ትዕዛዝ ሲታጠፍ ታዝበናል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሱትን ህገወጥ ተግባሮች በአንክሮ በመከታተል በየጊዜው ጩኸቱን ከማሰማቱም ባሻገር አባላቱም ጭምር የዚህ ህገ ወጥ ተግባር ተጠቂዎች በመሆናቸው በፍርድ ቤት በአጠቃላይ በህግ ላይ እየተደረገ ያለውን ጉዳይ ቀዳሚ ምስክር ነው፡፡
semayawi Party
የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ የሺዋስ አሰፋና ከእሱ ጋር በአንድ መዝገብ የተከሰሱ ፖለቲከኞችና ሌሎች ዜጎች ያለ ምንም መረጃ ቤታቸው ተበርብሮ ታስረው በማዕከላዊ፣ በቂሊንጦና በኋላም በቃሊቲ እስር ቤቶች ከፍተኛ ሰብአዊ መብት ጥሰት ደርሶባቸዋል፡፡ እነ የሺዋስ በእየ እስር ቤት የሚደርስባቸውን በደል ለፍርድ ቤቱ ቢያመለክቱም ሰሚ ከማጣትም ባሻገር ‹‹ችሎት ደፈራችሁ›› ተብለው ለተጨማሪ ቅጣት ተዳርገዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ያለ ምንም መረጃ የታሰሩትን ነፃ ናቸው ቢልም በካድሬ ትዕዛዝ የማረሚያ ቤቱ ፖሊስ ከእስር ቤት እንዳይወጡ በማገዱ፣ ይግባኝ ቢጠየቅ እንኳ ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው መከታተል እየቻሉ በአስከፊው እስር ቤት እየማቀቁ ይገኛሉ፡፡

በተጨማሪም መንግስት ራሱ በጠራው ሰልፍ ሰበብ ባልተገኙበት፣ የተገኙትንም በፈጠራ ክስ እየለቀመ ያሰራቸው የፓርቲያችን አባላትና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ከ6 ወር በታች በማያሳስር ክስ እስከ አራት አመት ተወስኖባቸው፣ አብዛኛዎቹም አሁንም ድረስ ምንም አይነት ፍትህ ሳያገኙ በእስር ቤት እየተንገላቱ ይገኛሉ፡፡ በሰልፉ ሰበብ ከታሰሩት መካከል አባላችን ናትናኤል ያለምዘውድ 3 አመት ከ3 ወር ሲፈረድበት፣ ብሌን መስፍን፣ ማቲያስ መኩሪያ፣ ተዋቸው ዳምጤ ከ6 ወር በታች በሚያሳስር የፈጠራ ክስ ተከሰው አሁንም ድረስ ፍትህ ሳያገኙ በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ እነ ብሌን በተደጋጋሚ በመከላከያ መረጃነት የሚያገለግላቸውንና አቃቤ ህግም አለኝ ያለውን የቪዲዮ ማስረጃ እንዲቀርብላቸው ቢጠይቁም ሊቀርብላቸው አልቻለም፡፡ ይባስ ብሎ ማረሚያ ቤቱ ‹‹መጓጓዧ መኪና ስለሌለን ነው›› በሚል ለምክንያትነት እንኳ መቅረብ በማይገባው ሰበብ በቀጠሯቸው እንዳይቀርቡ በማድረግ ለተጨማሪ ጊዜያት በእስር ላይ እንዲቆዩ እየተደረጉ ይገኛሉ፡፡ አቶ አለነ ማህፀንቱ አንዱ ፍርድ ቤት በዋስ ሲለቀው በደህንነቶች እየተያዘ አሁንም ድረስ በእስር ላይ ይገኛል፡፡ ሌሎችም የመኢአድና የአንድነት አባላት የነበሩ በተመሳሳይ የፍርድ ሂደታቸው ሆን ተብሎ እንዲጓተት እየተደረገ ይገኛል፡፡

አገዛዙ ሰማያዊን ለማዳከም በተለያዩ አካባቢዎች እየታደኑ የሚታሰሩት የፓርቲ አመራሮቻችንም በተመሳሳይ ሁኔታ ህግ ተነፍጓቸው በእስር ቤት ይገኛሉ፡፡ ባህርዳር ላይ ታስረው የሚገኙ የፓርቲያችን 7 አመራሮች የ15 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ፍርድ ቤቱ ቢወስንም እንደተለመደው ካድሬዎች የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ሽረው በእስር ቤት እንዲቆዩ አድርገዋል፡፡ ሽዋሮቢትና ጎንደር ላይም በርካታ የፓርቲያችን አባላትና አመራሮች ለወራት የታሰሩበት ሳይታወቅ ከቆዩ በኋላ ወደ ማዕከላዊ ተዛውረው ቤተሰብ እንዳይጠይቃቸው ተደርገዋል፡፡

ይህ ፓርቲውን የማዳከም የአገዛዙ ህገ ወጥ እርምጃ አሁንም የቀጠለ ሲሆን ከሳምንት በፊት በአርባ ምንጭ የሰማያዊ ፓርቲ አደራጆችን፣ አባላትንና ቤተሰቦቻቸውን በሀሰተኛ ክስ እስከማሰር ደርሰዋል፡፡ ከታሳሪዎች መካከል የጋሞ ጎፋ ዞን አስተባባሪ የሆነው አቶ ሉሉ መሰለና ቤተሰቦቹ ከሌሊቱ 8 ሰዓት ቤታቸው ተበርብሮ ሲታሰሩ፣ በእስር ላይ የሚገኘው የሰማያዊ ፓርቲ የዞኑ አስተባባሪ አቶ በፍቃዱ አበበ የ65 አመት አዛውንት እናቱ እና እህቱም ታስረው፡፡ አብዛኛዎቹ የዜጎች ሰብአዊ መብት ወደሚገፈፍበትና ጭካኔ ወደሚፈፀምበት ማዕከላዊ እስር ቤት ተዛውረዋል፡፡

የፍትህ ስርዓቱ ለአገዛዙ መግዢያ፣ ፍርድ ቤትም በተራ ካድሬ የሚታዘዝ በመሆኑም ከመቼውም ጊዜ በላይ ህግ ከእነ ካባዋ ተቀብራለች፡፡ ለይስሙላ የተቀመጠው ህግ እስረኞች በቤተሰቦቻቸው፣ በህግ አማካሪዎቻቸው፣ በእምነት አባቶቻቸውና በሌሎችም መጠየቅ እንዳለባቸው ዓለም አቀፍ የሆኑትን የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች ጠቃቅሶ ቢያስቀምጥም በእውኑ ግን እነ እስክንድር ነጋ፣ አንዱዓለም አራጌ፣ ተመስገን ደሳለኝ እና አሁንም በእስር ላይ የሚገኙት በርካታ አባላቶቻችንና ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች እንዳይጠየቁ ተከልክለዋል፡፡ ምግብ እንዳይገባላቸው ይደረጋል፡፡ እስር ቤቱ የሚያደርስባቸውን በደል ለፍርድ ቤት በሚያመለክቱበት ጊዜው ጨለማ ቤት ውስጥ እየታሰሩና እየተደበደቡ ነው፡፡

የፓርቲያችን አባላትና ሌሎች ዜጎች በተለያዩ ጊዜያት ያለ መረጃ ታስረው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እንደተያዘ አገዛዙና በስሩ የሚገኙት ሚዲያዎች ከፍርድ ቤቱ በፊት አጥፊዎች ተብለው ተፈርዶባቸዋል፡፡ ያለ መረጃ በመታሰራቸውና በመከሰሳቸው ይኼው ካድሬ የሚያዘው ፍርድ ቤት ነፃ ሲላቸውም ፖሊስ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ጥሶ እስር ቤት ውስጥ እያከረማቸው ይገኛል፡፡ አገዛዙ የሚደርስበትን ጫና በህግ ሥም ለማቃለልና ህግን ለመግዢያነት እንደሚጠቀምም ያለ ምንም መረጃ ታስረው መረጃ ስላልተገኘባቸው ከበርካታ ስቃይ በኋላ የተለቀቁትን ማስታወስ በቂ ነው፡፡ ለአብነት ከአንድ አመት ስድስት ወር በኋላ በስቃይ እስር ቤት የቆዩት የዞን ዘጠኝ አባላት እና አሁንም በፖሊስ ትዕዛዝ እስር ቤት እንዲቆዩ የተደረጉትን እነ የሺዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ አብርሃ ደስታና ዳንኤል ሺበሽ በታፈነው ፍርድ ቤት እንኳ ነፃ መባላቸው ለፀረ ሽብር ህጉና ሌሎች የመግዢያ ህጎችን ያጋለጠና ፍትህ እንደተቀበረች በግልፅ አሳይቷል፡፡

በአጠቃላይ ዜጎችን ያለ መረጃ አፍኖ ማሰር፣ በቀጠሯቸው አለማቅረብ፣ እንዳይጠየቁ እና ምግብና ሌሎች ቁሳቁሶች እንዳይገቡላቸው መከልከል፣ በፍርድ ቤት ነፃ የተባሉ ይግባኝ ቢጠየቅባቸው እንኳ ከእስር ቤት ውጭ ሆነው መከራከር እየተገባቸው ከእስር እንዳይለቀቁ ማድረግና ሌሎችም በህገ መንግስቱና በአዋጆች አገዛዙ የደነገጋቸውን ሳይቀር መጣሱ በኢትዮጵያ ህግ ለፖለቲካው መሳሪያ እንጅ የበላይነት እንደሌለ ከበቂ በላይ ማስረጃ ነው፡፡ አንድ ሀገር እንደ ሀገር ለመቀጠል፣ ዜጎችም ሀገር አለን ብለው ለመኖር ህግ ትልቅ ነገር እንደመሆኑ አገዛዙ ፍትህ ሥርዓቱን ለራሱ በሚመቸውና በሚጠቅመው መንገድ እየዘወረ ኢትዮጵያንና ዜጎቿን ለባሰ አደጋና ስቃይ እየዳረገ እንደሆነ ተገንዝበናል፡፡ ስለሆነም በኢትዮጵያ ህጋዊ ሥርዓት እንዲመሰረትና የህግ የበላይነት እንዲከበር ሰማያዊ ፓርቲ ትግሉን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ ይህን ትግላችንን ከዳር ለማድረስ የሚመለከታቸው የፖለቲካ ኃይሎች፣ የኢትዮጵያ ህዝብና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ከጎናችን እንዲቆም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
ጥቅምት 24/2008 ዓ.ም
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/48013#sthash.zGEsfXeN.dpuf

አርበኞች ግንቦት 7 ለሁለተኛ ጊዜ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሠራዊት አሰመረቀ * ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ንግግር አድርገዋል



dr birhanu
birhanu nega
አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ለሁለተኛ ጊዜ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት አስመረቀ፡፡
አርበኞች ግንቦት 7 በሁለት ድርጅቶች ማለትም በኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር እና በግንቦት 7 ንቅናቄ ውህደት ጥር 2 ቀን 2007 ዓ.ም ከተመሰረተ በኋላ ከትናትና በፊት እሁድ ዕለት ጥቅምት 7 ቀን 2008 ዓም ለሁለተኛ ጊዜ ብዛት ያላቸውን አርበኛ ታጋዮች ለሦስት ወራት አሰልጥኖ አስመርቋል፡፡
እነዚህ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሁለተኛ ዙር ተመራቂ አርበኛ ታጋዮች ለሦስት ተከታታይ ወራት የተሰጣቸውን የፖለቲካ፣ የወታደራዊ እና ሌሎች ተያያዥ የሆኑ የመረጃና ደህንነት ትምህርቶችን በሚገባ ወስደው በሁሉም መስክ አመርቂ ውጤት በማስመዝገብ ነው ሊመረቁ የቻሉት፡፡
እጅግ በጣም ደማቅ በሆነ ስነ-ስርዓት በተከናወነው የምረቃ በዓል ላይ ከተለያዩ ቦታዎች ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች የታደሙ ሲሆን የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር አርበኛ ታጋይ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የድርጅቱ የትምህርትና ስልጠና መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ታጋይ ተስፋሁን ተገኝ ንግግር በማሰማት ለተመራቂ አርበኛ ታጋዮች መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ከውህደቱ ኋላ የመጀመሪያውን ዙር ሰልጣኞች ያስመረቀው ግንቦት 2 ቀን 2007 ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል፡፡
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47561#sthash.byLB3xXt.dpuf

በስዊድን ለአርበኞች ግንቦት ሰባት መርጃ ገንዘብ ተሰበሰበ

by jeri Emeru


አቶ ዘለሌ ፀጋ ስላሴ ዝግጅቱን ሲከፍቱ
አቶ ዘለሌ ፀጋ ስላሴ ዝግጅቱን ሲከፍቱ

ቅዳሜ ኦክቶበር 31 -2015 (ጥቅምት 20 – 2008 ዓ.ም ) በስዊድን ዋና ከተማ በስቶክሆልም ለአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ መርጃ የሚሆን የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ተደረገ። በዝግጅቱ ላይ በርካታ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ተገኝተዋል።በቦታው ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት አቶ አበበ ቦጋለ  የውጪ እንቢተኝነት ሊቀመንበር እና አቶ ቸኮል ጌታነህ የንቅናቄው ከፍተና አመራር ናቸው።
አቶ አበበ ቦጋለ ንግግር ሲያደርጉ
አቶ አበበ ቦጋለ ንግግር ሲያደርጉ

ዝግጅቱ ረፋዱን 14፡00 ሰዓት የተጀመረ ሲሆን አቶ ጌታሁን ማሬ የዝጅቱ አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ  የስዊድን የአርበኞች ግንቦት ሰባት የስራ አስፈጻሚ ሰብሳቢ የሆኑትን አቶ ዘለሌ ፀጋ ሥላሴን ስለዝግጅቱ ገለጻ እንዲያደርጉና ዝግጅቱንም እንዲመሩ  ጋብዘዋል። አቶ ዘለሌ በበኩላቸው የከተማው የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ያለበትን ሁኔታ ገልጸው እንግዶቹንም በማስተዋወቅ አቶ አበበ ቦጋለና አቶ ቸኮል ጌታሁን ንግግር እንዲያደሩ ጋብዘውል።
አቶ ቸኮል ጌታሁን ንግግር ሲያደርጉ
አቶ ቸኮል ጌታሁን ንግግር ሲያደርጉ
አቶ አበበ በአሁኑ ሰዓት አርበኞች ግንቦት ሰባት እየሰራ ስላለው የስራ ክንውን እቅድና አላማ እንዲሁም ደጋፊዎቹና አባላቶቹ እያደረጉ ስላሉት እንቅስቃሴ ማብራሪያ ሰጥተዋል። አቶ ቸኮል ጌታሁን በበኩላቸው በኤርትራ ቆይታቸው ወቅት ስለተመለከቱት የአርበኛው ቆራጥነትና የአላማ ጠንካራነት የገለጹ ሲሆን በአሁን ሰዓት የድሮ ጀግናችን ስም  በመጥራት የምንቀመጥበት ጊዜ ሳይሆን እኛው እነሱን ተክተን በጀግንነት ስማችን ማስጠራት የሚገባን ጊዜ ነው  በማለት ደጋፊውንና አባላትን የሚአበረታታና የሚነሳሳ መል ክት አስተላልፈዋል።
ከሁለቱ አመራሮች ንግግር በኋላ ተሰብሳቢው ሰው ጥያቄ እንዲያቀርብ ተጋብዞ ለቀረቡት ጥያቄዎች መልስ ተሰጥቷል። እንዲሁም ንቅናቄውን በተመለከተ ግልጽ ውይይት ተደርጓል። ከዚህ በመቀጠል « በደል ይረሳል ወይ?» የሚል ግጥም በማራኪና በወለላዬ ከቀረበ በኋላ  የገቢ ማሰባሰቢያ ጨረታ ተደርጓል። ለጨረታ የቀረበው የንቅናቄው ሊቀመንበር የሆኑት የፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ቆራጡ አርበኛ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከሚመሯቸው አርበኞች ጋር ሆነው የሚታዩበት «ላንቺ ነው ኢትዮጵያ » የተባለ ምስል ሲሆን ይሄው ምስል በግልና በቡድን ተጫርቶ ከፍተኛ ፉክክር ከተደረገ በኋላ  በአንድ መቶ አራት ክሮነር( የስዊድን ገንዘብ ) የስዊድን የስደተኞች ማህበር አሸንፎ ምስሉን የግሉ አድርጎታል። ከዚህ ከጨረታ ከተገኘው ገንዘብ ሌላ ሁለት የቃል ኪዳን ቀለበቶች የመግቢያ ገንዘብ ሦስት መቶ ዶላርና ከእጣ የተሰበሰበ ገቢ ተገኝቷል።
የጨረታው አሸናፊዎች
የጨረታው አሸናፊዎች
በወቅቱ በስደተኛ ማህበሩ አባላት ይደረግ የነበረው ተሳትፎ ዝግጅቱን አድምቆት አርፍዷል በጨረታው ጊዜም በማሃል እረፍት በሚደረግበት ወቅት የ/ሪት ሙሉቀን አማረ «ኢትዮጵያዊት ነሽ አትበሉኝ » የሚል ግጥምና  የ/ሮ ውቤ ማሞ እንዲሁም የአቶ መብራቱ ፀሐዩ  ቀስቃሽ ግጥሞች  ቀርበዋል።
የጨረታው አሸናፊዎች በተቀበሉበት ወቅት
የጨረታው አሸናፊዎች በተቀበሉበት ወቅት
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47992#sthash.2DbljgmM.dpuf

måndag 2 november 2015

See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47912#sthash.DVhGjt6k.dpuf

የፓርላማው ድራማ –  ይገረም ዓለሙ





ሙሉ በሙሉ በአብዮታዊ ዴሞክራቶች በመያዙ የተለየ ሀሳብ የማይሰማበት ሙት የሆነውን ፓርላማ ህይወት ያለው ለማስመሰል የተዘጋጀው ድራማ ማክሰኞ ጥቅምት 16/2008 መታየት ጀምሯል፡፡ ይህ የፓርላማ ድራማ  ቤቴሌቭዥን እንደምናያቸው ድራማዎች ሰሞነኛውን ትኩሳት እየተከተለ በየሳምንቱ የሚጻፍና የሚዘጋጅ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ በዚህ የመጀመሪያ ቀን ትዕይንት መሪ ተዋናይ ሆነው የቀረቡት ጠቅላይ ምኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ  ከፓርላማው አባላት መካከል  በተመረጡት ተዋንያን እየተጠየቁ በመመለስ ሲተውኑ ታይተዋል፡፡

ከቀደሙት ጠቅላይ ምኒስትር ጀምሮ ሲነገር እንጂ ሲተገበር የማይታየው ከተቀዋሚዎች ጋር አብሮ የመስራት ጉዳይ ለመጀመሪያው ቀን ድራማ ማድመቂያነት ከተመረጡት ጉዳዮች አንዱ ነበር፡፡ ተባብሮ መስራት ማለት እንደ ተቀዋሚዎች  በመሰረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በመነጋገር ሀገራዊ መግባባት ከመፍጠር የሚጀምር  እንደ ወያኔ ደግሞ እሱ በሚፈልገው ጉዳይ ሲፈልጋቸው ብቻ በመጥራት የሚገለጽ ነው፡፡ እንዲ ሆነናም  በአምስት ዓመቱ ዕቅድ ላይ ለማወያየት  ምርጫ ቦርድ መዝግቦ ለሚያውቃቸው ፓርቲዎች በሙሉ መንግጨሥታቸው ሰነድና ደብዳቤ መላኩን የገለጹት አቶ ኃይለማሪያም ብዙዎቹ በስብሰባው ላይ ሲገኙ ጥቂቶች ውኃ የማይቋጥር ምክንያት በመስጠት አልተገኙም አሉ፡፡ ያልተገኙት ፓርቲዎች ያቀረቡት ምክንያት ውኃ የማይቋጥር ነው ያሉበትን ምክንያትም ሲያረዱ በሕጋዊ መንግድ የተመረጠ መንግሥት ስላልሆነ ከእርሱ ጋር አንነጋርም ማለታቸው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ለመሆኑ ጥሪያችንን ተቀብለው ብዙዎቹ ተገኝተዋል የተባሉት  ፓርቲዎች የትኞቹና እነማን ናቸው፡፡ዝቅ ብለን እናያቸዋለን፡፡

የመሳሪያ ትግል የሚያካሂዱትን ድርጅቶች አስመልክቶም ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ  ለራሱም መሆን ካልቻለው ሻዕቢያ ጋር ሆነው የሚያመጡት ውጤት ስለማይኖር ጊዜያቸውን በከንቱ ባያባክኑ በማለት ምክር ለመስጠት የዳዳቸው አቶ ኃይለማሪያም አንዳንዶቹ እኮ ጭራሽ የሌሉ ናቸው በማለት ኦነግን ኦብነግንና የጋምቤላ ህዝቦች ንቅናቄን ጠቀሱ፡፡ ይቺ ገለጻ የቀረበችው በደራሲውና  አዘጋጁ ስህተት ይሁን ወይንም በርሳቸው የጥናት ጉደለት ባይታወቅም ሁለት መልእክት ታስተላልፋለች፡፡ አንደኛ እነዚህ የተጠቀሱት ድርጅቶች ሰሞኑን ተባብረው ለመስራት የደረሱበት ስምምነት እነ አቶ ኃይለማያም ሰፈር የፈጠረው ነገር መኖሩን እንድንጠረጥር ያሚያደርግ ፣ ሁለተኛ ደግሞ በሰሜን በኩል ድምጻቸው የሚሰማው ድርጅቶች እነዚህ ብቻ አይደሉምና ለሌሎቹ መኖሮና ጠንካራ መሆን በዘወርዋራ እውቅና የሰጠ ነው፡፡

አቶ ኃይለማሪያም የአቶ መለስ ሌጋስ አስቀጣይ እንደመሆናቸው ስለ ድርጅቶቹ የተናገሩት ከርሳቸው የወሰዱትን ነው፡፡ አቶ መለስ ብረት አንስተው መንግሥታቸውን የሚታገሉ ድርጅቶችን አስመልክቶ ሲላቸው አጥፍተናቸዋል የሉም ሲሉ ሌላ ግዜ ደግሞ በግላቸው ብዙ ርቀት ሄደው ከድርጅቶቹ መሪዎች ጋር ለመገናኘትና ለመደራደር እንደጣሩ ሲናገሩ ሰምተናል፡፡ ሌላ ግዜ ደግሞ ወድመዋል ተደምስሰዋል የተባሉት ደርጅቶች በዚህ ቦታ እንዲህ አደረጉ ጥፋት አደረሱ የሚል ዜና ስንሰማ ኖረናል፡፡ የሉም በተባሉ ድርጅቶች ስምም ዜጎች እየተወነጀሉ ታስረዋል እየታሰሩም ነው፡፡ አቶ መለስ አይደለም የሀገር ውስጥ ተፋላሚዎችን ሶማሌ ተሻግረው አልሻባብን ድምጥማጡን አጥፍተነዋል ብለውንም ነበር፡፡

አቶ ኃይለማሪያም ባያስታውሱም እኛ አንረሳውም፡፡ አቶ መለስ ከርሳቸው ፍላጎት ውጪ ስንዝር መሄድ የማይችለውን ፓርላማ አስፍቅደው(ነግረው)  እንዲህ አስታዋሽ አጥቶ የቀረውን ሰራዊት  ሶማሊያ በላኩበት ወቅት  የገጠማቸውን ተቃውሞ ዝም ለማሰኘት  ሰራዊታችን አልሻባብን ደምስሶ አሁን የቀረው ቃርሚያ ብቻ ነው፣ ያንን አጠናቆ በቅርብ ቀን ይመለሳል ብለውን ነበር፡፡ ነገር ግን ይኸው እስካሁን አልሻባብም አልጠፋ ሰራዊቱም አልተመለሰ፡፡ እንደውም በተቃራኒው ወንድሞቻችን የአልሻባብ ጥቃት ሰለባ እየሆኑ ነው፡፡  አቶ ኃለማሪያም እኔም አንደ መለስ ብለው በንቀት ስሜት የሉም ጠፍተዋል ስላሉዋቸው ድርጅቶች መረጃ ስለሌለኝ የምለው አይኖርም፤ የላችሁም የተባላችሁ መኖራችሁን አሳይዋቸውና አቶ ኃይለማሪም በዚህ አፋቸው ምን እንደሚሉ ለመስማት አብቁን የሚለው ግን መልእክቴ ነው፡፡

አቶ መለስ የሻዕቢያና ወያኔ ጸብና ፍቅር ለወላይታው ምኑ ነው ብለው ለአቶ ኃይለማሪያም አለነገሯቸው እንደሁ እንጂ ወያኔን አዲስ አበባ ያደረሰው ለራሱም የማይሆን ያሉት ሻዕቢያ ነው፡፡ ይህም  ብቻ  አይደለም ሌላው ኢትዮጵያዊ (የወያኔ ታጋይ ጭምር ) የማይታመን ሆኖ እስከ ተጣሉበት ግዜ ድረስ ቤተ መንግሥቱ ይጠበቅ የነበረው በሻዕቢያ ሰራዊት እንደነበረ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ስለሆነም አቶ ኃይለማሪያም ወያኔዎች ስለ ሻዕቢያ ዛሬ የሚሉትን ብቻ እየተቀበሉ መናገር ሳይሆን ትናንት ምን ይሉ ምንስ ያደርጉ እንደነበር የተጻፈ አንብበው የነበረ ጠይቀው ቢናገሩ ቢያንስ ጠቅላይ ምኒስትር ለሚለው ማዕረጋቸው( ይስሙላም ቢሆን) የሚመጥን ይሆናል፡፡

ከላይ እንደተገለጸው አቶ ኃይለማሪያም ስለ አብሮ መስራት ሲናገሩ ምርጫ ቦርድ የመዘገባቸውን ፓርቲዎች በሙሉ ጠርተን አብዛኛዎቹ ተገኝተዋል ነው ያሉት፡፡ አብዛኛው የሚለው የጥቅል መጠሪያ  ለወያኔም ለፓርቲዎቹም ለምርጫ ቦርድም እያገለገለ ነው፡፡ እነዚህ ፓርቲዎች በቁጥር ሲገለጹ እንጂ በስም ሲጠሩ አይሰማም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ምርጫ ቦርድ መዝገብ ላይ ሰፍረው የሚገኙት አንዳንዶቹ የሌሉ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ  ምርጫ ሲመጣ ብቻ ብቅ የሚሉና ለምርጫ የሚሰጣቸውን ገንዘብ ተቀብለው የአጃቢነት ሚናቸውን ተወጥተው ለአራት ዓመት የሚጠፉ ናቸው፡፡ ጥቂቶቹም ፓርቲ ለመባል የሚያበቃ ቁመና የሌላቸው አቶ በረከት የፓርቲዎቹ ጥቅማቸው አልታይ ብሉአቸው ይሁን ስሜት ገፋፍቶአቸው ወይንም እውነት ተናንቆአቸው ባይታወቅም በመጽሀፋቸው የቤተሰብ ፓርቲ ሲሉ  የገለጹዋቸው ናቸው ፡፡  በርግጥ ለመናገር አንዳንዶቹ ሊቀመንበር ተብሎ ከሚጠራው ሰው ቀጥሎ የሚጠራ ሶስትና አራት ሰው የሌላቸው በመሆኑ የቤተሰብ ፓርቲ የሚለውንም አያሟሉም፡፡ ብዙዎቹ ከተባሉት ከእነዚህ ስመ ፓርቲዎች ውስጥ  ብዙዎቹን እንኳን ህብረተሰቡ ምርጫ ቦርድም አያውቃቸው፡፡ ድረ ገጹን ብትጎበኙ ቦርዱ ስለማያውቃቸው የተመዘገቡበትን ቀን መሙላት አቅቶት  ቦታው ክፍት ሆኖ ታገኙታላችሁ፡፡ ፤ብቻ ብዙዎች እየተባሉ ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ይውላሉ፡፡እነዚህን በስም እየጠቀሱ መሪ የሚባሉትን ሰዎች ምንነትና ማንነት እያሳዩ መግለጽ የሚቻል ቢሆንም የሚፈይደው ነገር የለም፡፡ የምርጫ ቦርድን ድረ ገጽ ከጎበኙ  ሌላም ነገር ይታዘባሉ፣ ምርጫ የማስፈጸም ብቃት አለው ተብሎ ምስጋና የተዥጎደጎደለት ይህ ተቋም ድረ- ገጹን ወቅታዊ ማድረግ ተስኖት ከአስር ዓመት በፊት የነበረ መረጃ ነው የሚያገኙት፡፡

ፓርቲ ማለት በምርጫ ቦርድ ተመዝግቦ የህጋዊነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የተሰጠው ነው ካልተባለ በስተቀር  ብዙዎች የሚባሉት ከወያኔ ዳረጎት እየተቀበሉ፤ በምርጫ ቦርድ መልካም ፈቃድ ፓርቲ እየተባሉ፤ በአዳማቂነትና በአጃቢነት  የሚያገለግሉ፣ እንኳን አባል የተሟላ አመራር የሌላቸው ናቸውና ፓርቲ ሊባሉ የሚበቁ አይደሉም፡፡ መሪ ለሚባሉት ሰዎች ግን የእለት እንጀራም የሕይወት መንገድም ሆኖ እየጠቀማቸው ነው፡፡ በአንጻሩ ብዙም ባይሆን ለወያኔ ዕድሜ መርዘምም እየረዱ ነው፡፡ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግን ኖሩም አልኖሩ “ተለበሰ ቀረ የደበሎ ቅዳጅ ”እንደሚባለው ናቸውና ምንም ፋይዳ የላቸውም፡፡ እንደውም የማይቻል ሆኖ እንጂ አለመኖራቸው ይሻል ነበር፡፡

ሙቱን ፓርላማ ህይወት ያለው ለማስመሰል የተጀመረው ድራማ  ደራሲና አዘጋጁ ሰልችቶአቸው እስካላቆሙት ድረስ በጀመረው መልኩ ወቅታዊ የትኩረት አቅጣጫዎችን እየተከተለ የሚቀጥል ይሆናል፡፡ የእኛም ማየትና መስማት ብሎም ከምናይ ከምንሰማው ተነስተን ብዕር ከወረቀት ማገናኘት እንዲሁ ይቀጥላል፡፡እስካላቆሙት ድረስ ያልኩት አቅጣጫ ለማስቀየሻ እየተባሉ በዚህ መልኩ የሚጀመሩ ጉዳዮች ሲዘልቁ ስለማይታይ ነው፡፡ደግሞስ የማስመሰል ስራ መች ብዙ መንገድ ያስኬዳል፡፡ይህ የፓርላማ ድራማ ቀልቡን የሚስበው ሰው ኖር ይሆን!

-


fredag 30 oktober 2015

- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47777#sthash.EXqT2pP1.dpuf

ሚያ ቤት እነ አብርሃ ደስታና ሃብታሙ አያሌውን ፍርድ ቤት ባለማቅረቡ ዳኞች ውሳኔ ሳይሰጡ ቀሩ







በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
የሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸው በፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ እንዲሰናበቱ የተበየነላቸው የአንድነት፣ የሰማያዊ እና የአረና ፓርቲዎች አመራሮች ላይ አቃቤ ህግ ይግባኝ ጠይቆ ጉዳያቸው በጠቅላይ ፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙት አምስት ተከሳሾች ለጥቅምት 22/2008 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል፡፡

ዛሬ ጥቅምት 17/2008 ዓ.ም የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ቢጠበቅም ማረሚያ ቤት ሳያቀርባቸው በሌሉበት ቀጠሮ የተሰጣቸው የፓርቲዎች አመራሮቹ ሀብታሙ አያሌው፣ የሺዋስ አሰፋ፣ አብርሃ ደስታ፣ ዳንኤል ሺበሽ እና አብሯቸው ይግባኝ የተጠየቀበት አብርሃም ሰለሞን ናቸው፡፡

የቂሊንጦ እና የቃሊቲ ማረሚያ ቤቶች እነ ሀብታሙን ፍርድ ቤት ያላቀረቡበትን ምክንያት ፍርድ ቤቱ ሲጠይቅ፣ ‹‹ቃሊቲ በፕላዝማ ይታያል ስለተባለ አላመጣናቸውም፤ ከአይ.ሲ.ቲ ጋር ተነጋግረው ነው ያስቀሯቸው›› የሚል መልስ ተሰጥቷል፡፡ ማረሚያ ቤቱ እነ ሀብታሙን ብቻ ሳይሆን በሌላ መዝገብ በተለያዩ ወንጀሎች ስር የተጠቀሱ ተከሳሾችንም አለማቅረቡ ታውቋል፡፡

ፍርድ ቤቱ በበኩሉ የቃሊቲ ማረሚያ ቤትን መልስ ካደመጠ በኋላ፣ ‹‹ይሄ ቪዲዮ ኮንፈረንስ የሚባል ነገር የሚሆን አይደለም፤ አቅርቧቸው ብለን አዝዘን ነበር፤ እኛ ነን የምናዝዛችሁ ወይስ ማን ነው? አሁንም ቀጣይ ቀጠሮ ላይ አቅርቧቸው›› ሲል በእነ ሀብታሙ መዝገብም በሌሎች መዝገቦችም ላይ ዛሬ ላልቀረቡ ተከሳሾች ተመሳሳይ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ በመሆኑም እነ ሀብታሙ አያሌው ሰኞ ጥቅምት 22/2008 ዓ.ም የተጠየቀባቸው ይግባኝ ያስቀርባል ወይስ አያስቀርብም የሚለውን ብይን ቀርበው ለመስማት ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል፡፡

Related Posts:በእነ ሀብታሙ አያሌው ላይ ተረኛ…

- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47777#sthash.EXqT2pP1.dpuf


torsdag 29 oktober 2015

5 ብሔር ተኮር ነፃ አውጪ ግምባሮች በጋራ የነፃነት እና የዴሞክራሲ ንቅናቄ መሠረቱ


(ዘ-ሐበሻ) በኦስሎ ኖርዌይ ከኦክቶበር 22 እስከ ኦክቶበር 23, 2015 ዓ.ም በተደረገ የጋራ ጉባኤ 5 የኢትዮጵያ የብሄር ድርጅቶች በጋራ ለመታገል አዲስ ንቅናቄ መመስረታቸውን ለዘ-ሐበሻ በላኩት መግለጫ አስታወቁ::
olf ONLF
ጥምረቱን የመሰረቱት የቤኒሻንጉል ነፃ አውጪ ንቅናቄ; የጋምቤላ ነፃ አውጪ ንቅናቄ; የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግምባር; የኦሮሞ ነፃነት ግምባርና የሲዳማ ብሔራዊ ነፃነት ግምባር ሲሆኑ የኢትዮጵያ ያለውን ስርዓት በጋራ ጥለው የሁሉንም ብሄሮች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት የሚያከብርና የአንድን ቡድን የበላይነት እንዲያበቃ የሚያደርግ ስርዓት ለመፍጠር እንደሚታገሉ በመስራች ጉባኤያቸው መጨረሻ ላይ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል::
ሃገሪቱን ወደ ተሻለ የፖለቲካ ሽግግር ቀርጸው ለመንቀሳቀስ የተሰማሙት እነዚሁ 5 ድርጅቶች የአዲሱ ጥምረታቸው መጠሪያ የሕዝቦች ጥምረት ለነፃነትና ለዴሞክራሲ (Peoples Alliance for Freedom and Democracy (PAFD) ተብሎ ተሰይሟል::
አርበኞች ግንቦት በቅርቡ ከአማራው ንቅናቋ; ከአፋር ንቅናቄና ከትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ጋር በጋራ ለመታገል ጥምረት መፍጠሩ ይታወሳል:: ትናንት በኖርዌይ ጥምረታቸውን ያወጁት የቤኒሻንጉል ነፃ አውጪ ንቅናቄ; የጋምቤላ ነፃ አውጪ ንቅናቄ; የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግምባር; የኦሮሞ ነፃነት ግምባርና የሲዳማ ብሔራዊ ነፃነት ግምባር ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር ወደፊት ስለሚፈጥሩት የጋራ ጥምረት ወይም ግንኙነት ይኑራቸው አይኑራቸው የተገለጸ ነገር ባይኖርም በቅርቡ ወደ ሚኒሶታ የመጡት የንቅናቄው የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ነአምን ዘለቀ “ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር እንዳለች እስካመኑ ድረስ ከሁሉም ጋር በጋራ ለመስራት እንችላለን::” ማለታቸውን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም::
ONLF and OLF

የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል፤ ጠ/ሚ/ር ኃይለማሪያም ደሳለኝና በኢትዮጵያ የእንግሊዝ ኤምባሲ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ያሉበትን ቦታ እንዲያሳውቁ ሊጠየቁ ነው


Share0  848  0 
 Share0
  • 848
     
    Share
Andargachew Tsige
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
በእነ ዘመነ ካሴ የክስ መዝገብ ከ2ኛ -5ኛ መዝገብ ለተከሰሱት አቶ አሸናፊ አካሉ (2ኛ ተከሳሽ)፣ አቶ ደናሁን ቤዛ (3ኛ ተከሳሽ)፣ አቶ ምንዳዬ ጥላሁን (4ኛ ተከሳሽ) እና አቶ አንሙት የኔዋስ (5ኛ ተከሳሽ) በመከላከያ ምስክርነት ተጠቅሰው በነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጉዳይ የልደታ ፍርድ ቤት 19ኛው ወንጀል ችሎት ለሶስት አካላት ትዕዛዝ እንዲሰጥ ተጠየቀ፡፡ የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ጥቅምት 12/2008 ዓ.ም አቶ አንዳርጋቸው እሱ ጋር እንደሌሉ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛው ወንጀል ችሎት በላከው ደብዳቤ መግለፁ ይታወሳል፡፡

ከ6ኛ-9ኛ ያሉት ተከሳሾች ማረሚያ ቤቱ በፈጠረው ችግር የአቶ አንዳርጋቸውን ምስክርነት ለመስማት የፍርድ ሂደታቸው እየተጓተተባቸው በመሆኑ የአቶ አንዳርጋቸው ምስክርነት ቀርቶ ብይን እንዲሰጥላቸው ሲጠይቁ 4ኛ ተከሳሽ አቶ ምንዳዬ ጥላሁን ‹‹ከአንዳርጋቸው ጋር ተገናኝተህ መመሪያ ተቀብለሃል ስለተባልኩ አቶ አንዳርጋቸው መጥቶ መመስከር አለበት›› ሲል አሁንም አቶ አንዳርጋቸው እንዲቀርቡለት ጥያቄውን አቅርቦ ነበር፡፡ ከአቶ ምንዳዬ ጥላሁን በተጨማሪ 3ኛ ተከሳሽ አቶ ደናሁን ቤዛም አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲመሰክሩለት በመፈለጉ፤ እና ፍርድ ቤቱም አቶ አንዳርጋቸው ይገኙበታል ተብሎ ለታሰበው ተቋም ትዕዛዝ ለመስጠት እንዲመቸው ተከሳሾቹ እንዲጠቁሙት በገለፀው መሰረት ተከሳሾቹ ፍርድ ቤቱ ለሶስት ተቋማት ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው በደብዳቤ ጠይቀዋል፡፡
negere
ሁለቱ ተከሳሾች ጥቅምት 15/2008 ዓ.ም ለፌደራል ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት በፃፉት ደብዳቤ የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን መያዙን በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንክ ኮርፖሬት መግለጫ መስጠቱን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ መስከረም ወር 2007 ዓ.ም የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌን መያዝ፣ የእድሜ ልክና የሞት ፍርደኛ መሆናቸውን በመግለፅ የኢትዮጵያ መንግስት ፍርዱን ተፈፃሚ እንደሚያደርግ መግለፃቸውን አስታውሰዋል፡፡ በተጨማሪም በኢትዮጵያ የእንግሊዝ ኤምባሲ አቶ አንዳርጋቸው ዜግነታቸው እንግሊዛዊ የሆሉትን አቶ አንዳጋቸው ጉዳይ ላይ ክትትል እንደሚያደርግ በደብዳቤው አስታወስዋል፡፡

በመሆኑም ከእነዚህ ሶስት አካላት በላይ አንዳርጋቸው ፅጌ ስላሉበት ቦታ የሚያውቅ ስለሌለ ለሶስቱም አካላት አቶ አንዳርጋቸው የት እንዳሉ እንዲገልፁና አቶ አንዳርጋቸውም ምስክር እንዲሆኑላቸው ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡

10 የፌ. ፖሊስ አባላት ኮንሶና ቦረና መገንጠያ ድልድይ ላይ ከነመኪናቸው ተደመሰሱ ሲል አርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ ዘገበ


Share1  446  3 
 Share1
  • 446
     
    Share
የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ራድዮ በሰበር ዜናው እንደዘገበው በላንድ ክሩዘር መኪና ተሳፍረው ወደ አርባ ምንጭ ከተማ በፍጥነት ያመሩ የነበሩ 10 የፌደራል ፖሊስ አባላት ኮንሶ እና ቦረና መገንጠያ ድልድይ ላይ ከነመኪናቸው ሙሉ በሙሉ ተደመሰሱ፡፡
ginbot 7እንደ ራድዮው ዘገባ በትናንትናው ዕለት አመሻሽ ላይ አስሩ የፌደራል ፖሊሶች መጀመሪያ አንድ አይሱዙ የጭነት መኪና በኃይል በማስገደድ አስቁመው የተሳፈሩ ሲሆን መኪናው መንቀሳቀስ ሲጀምር “የጫንካቸውን ፖሊሶች አራግፍ አለያ ከነንብረትህ አብረህ ትጋያለህ!” የሚል የስልክ ማስጠንቀቂያ መልዕክት ለአሽከርካሪው በመድረሱ አሽከርካሪው መኪናውን አቁሞ ፖሊሶቹን “አልሄድም” ይላቸዋል፡፡ ቀጥሎም ፌደራል ፖሊሶቹ ሾፌሩን ለማንገራገር ሞክረው ትዕዛዛቸውን በቀላሉ ሊቀበል ባለመቻሉ ስልክ ተደዋውለው ሌላ ላንድ ክሩዘር መኪና እንዲመጣላቸው በማድረግ ተሳፍረው ጉዟቸውን ቀጥለው ኮንሶ እና ቦረና መገንጠያ ድልድይ ላይ ሲደርሱ ቅፅበታዊ ጥቃት ተከፍቶባቸው ከነተሳፈሩበት መኪና ሙሉ በሙሉ ተደምስሰዋል ብሏል የአርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ::
ራድዮው ዘገባውን በመቀጠል የአርባ ምንጭ ከተማ ከፍተኛ ቁጥር ባለው የልዩ ኃይል እና የፌደራል ፖሊስ ጦር ተወራ ጓዳ ጎድጓዳዋ ሳይቀር እየታሰሰ ነው ብሏል::
ራድዮው እንደሚልው እየተፋፋመ ያለው የፀረ-ወያኔ ትግል እየተካሄደባቸው ከሚገኙት የደቡብ ኢትዮጵያ ከተሞች አንዷ አርባ ምንጭ መሆኗ እና በህወሓት የደህንነት ተቋም ጥርስ ውስጥ ገብታ አገዛዙ በአዓይነ ቁራኛ እየተከታተላት የምትገኝ መሆኗ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ከሰሞኑ ደግሞ አርበኞች ግንቦት 7 አንድ አይሱዙ ሙሉ የጦር መሳሪያ ወደ ከተማዋ አስገብቷል በሚል የህወሓት ልዩ ኃይሎች፣ ፌደራል ፖሊሶችና ደህንነቶች በየመንደሩ ተሰራጭተው ከፍተኛ አሰሳ እያደረጉ የነዋሪዎችን የዕለት ተዕለት የህይወት እንቅስቃሴና ሰላም በማወክ ላይ ናቸው፡፡
በተያያዘ ዜና ሙሉጌታ አባ፣ ፀጋዬ ገብረ ፃድቅ እና በኃይሉ ሲሳይ የተባሉ የህወሓት ጆሮ ጠቢዎችና የአካባቢው ቆራጭ ፈላጮች ፎቶግራፋቸው በማህበራዊ ሚዲያው መሰራጨቱን ተከትሎ ከትናንት ምሽት ጀምሮ አርባ ምንጭ ከተማ ከከዚህ ቀደሙ በባሰ ሁኔታ በፌደራል ፖሊስ ተጥለቅልቃ እየታመሰች ትገኛለች ሲል ራድዮው ዘግቧል::
ይህን ዜና የሚያስተባብል መረጃ ከመንግስት በኩል እስካሁን የተሰጠ ነገር የለም:: ዘ-ሐበሻ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ያደረገችው ሙከራም አልተሳካም::