torsdag 5 november 2015

በቡሬ ግንባር ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የህወሓት መራሹ መከላከያ ሰራዊት አባላት ከዱ



clash
(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ) ባጠቃላይ በአራቱም ማዕዘን የኢትዮጵያ ጠረፎች በቀበሮ ጉድጓድ ውስጥ የሚኖረው በህወሓት ቁጥጥር ስር የሚገኘው መከላከያ ሰራዊት አባላት በየዕለቱ ያለማቋረጥ ስርዓቱን እየከዱ ሲሆን በተለይም ደግሞ ከሰሞኑ ቡሬ ግንባር በስልጠና ላይ ይገኙ የነበሩ እጅግ በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወታደሮች ያገኙትን ቀዳዳ ተጠቅመው በቡድን በቡድን እየሆኑ በመሽሎክ ከአካባቢው ተሰውረዋል፡፡ ወሎ ውስጥ ከአንድ ቀበሌ ብቻ 10 ወታደሮች ከጦር ግንባር ከድተው ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡

አሁንም ቢሆን አብዛኛው ሰራዊት መሽሎኪያ ቀዳዳ እያነፈነፈ ሊከዳ በቋፍ ላይ እንደሚገኝ የመከላከያ ምንጮቻችን የላኩት መረጃ ያረጋግጣል፡፡

- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47951#sthash.oKSR1DMe.dpuf

ሰማያዊ ፓርቲ መግለጫ አወጣ – “ከነካባው የተቀበረውን የፍትህ ሥርዓት ነፃ ለማውጣት ትግላችን አጠናክረን እንቀጥላለን!”

(ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ)

ኢትዮጵያ ውስጥ ከህገ መንግስቱ ጀምሮ አዋጅና በሌሎችም የዜጎችን መብት የሚደነግጉ በርካታ መሰረቶች ቢኖሩም ለይስሙላ ህጋዊ ሥርዓት እንዳለ ከማስመሰልም አልፎ ለአገዛዙ ማጥቂያና መግዢያ ከመሆን ባለፈ የዜጎችን መብት እያስከበሩ አይደለም፡፡ ባለፉት 6 ወራት እንኳን ህግ እንደተቀበረች፣ በዚሁ አገዛዙ ውስጥ ተፅዕኖ ያለው የፍርድ ቤት አልፎ አልፎ የሚወስነው ውሳኔ በፖሊስ ቀጭን ትዕዛዝ ሲታጠፍ ታዝበናል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሱትን ህገወጥ ተግባሮች በአንክሮ በመከታተል በየጊዜው ጩኸቱን ከማሰማቱም ባሻገር አባላቱም ጭምር የዚህ ህገ ወጥ ተግባር ተጠቂዎች በመሆናቸው በፍርድ ቤት በአጠቃላይ በህግ ላይ እየተደረገ ያለውን ጉዳይ ቀዳሚ ምስክር ነው፡፡
semayawi Party
የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ የሺዋስ አሰፋና ከእሱ ጋር በአንድ መዝገብ የተከሰሱ ፖለቲከኞችና ሌሎች ዜጎች ያለ ምንም መረጃ ቤታቸው ተበርብሮ ታስረው በማዕከላዊ፣ በቂሊንጦና በኋላም በቃሊቲ እስር ቤቶች ከፍተኛ ሰብአዊ መብት ጥሰት ደርሶባቸዋል፡፡ እነ የሺዋስ በእየ እስር ቤት የሚደርስባቸውን በደል ለፍርድ ቤቱ ቢያመለክቱም ሰሚ ከማጣትም ባሻገር ‹‹ችሎት ደፈራችሁ›› ተብለው ለተጨማሪ ቅጣት ተዳርገዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ያለ ምንም መረጃ የታሰሩትን ነፃ ናቸው ቢልም በካድሬ ትዕዛዝ የማረሚያ ቤቱ ፖሊስ ከእስር ቤት እንዳይወጡ በማገዱ፣ ይግባኝ ቢጠየቅ እንኳ ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው መከታተል እየቻሉ በአስከፊው እስር ቤት እየማቀቁ ይገኛሉ፡፡

በተጨማሪም መንግስት ራሱ በጠራው ሰልፍ ሰበብ ባልተገኙበት፣ የተገኙትንም በፈጠራ ክስ እየለቀመ ያሰራቸው የፓርቲያችን አባላትና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ከ6 ወር በታች በማያሳስር ክስ እስከ አራት አመት ተወስኖባቸው፣ አብዛኛዎቹም አሁንም ድረስ ምንም አይነት ፍትህ ሳያገኙ በእስር ቤት እየተንገላቱ ይገኛሉ፡፡ በሰልፉ ሰበብ ከታሰሩት መካከል አባላችን ናትናኤል ያለምዘውድ 3 አመት ከ3 ወር ሲፈረድበት፣ ብሌን መስፍን፣ ማቲያስ መኩሪያ፣ ተዋቸው ዳምጤ ከ6 ወር በታች በሚያሳስር የፈጠራ ክስ ተከሰው አሁንም ድረስ ፍትህ ሳያገኙ በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ እነ ብሌን በተደጋጋሚ በመከላከያ መረጃነት የሚያገለግላቸውንና አቃቤ ህግም አለኝ ያለውን የቪዲዮ ማስረጃ እንዲቀርብላቸው ቢጠይቁም ሊቀርብላቸው አልቻለም፡፡ ይባስ ብሎ ማረሚያ ቤቱ ‹‹መጓጓዧ መኪና ስለሌለን ነው›› በሚል ለምክንያትነት እንኳ መቅረብ በማይገባው ሰበብ በቀጠሯቸው እንዳይቀርቡ በማድረግ ለተጨማሪ ጊዜያት በእስር ላይ እንዲቆዩ እየተደረጉ ይገኛሉ፡፡ አቶ አለነ ማህፀንቱ አንዱ ፍርድ ቤት በዋስ ሲለቀው በደህንነቶች እየተያዘ አሁንም ድረስ በእስር ላይ ይገኛል፡፡ ሌሎችም የመኢአድና የአንድነት አባላት የነበሩ በተመሳሳይ የፍርድ ሂደታቸው ሆን ተብሎ እንዲጓተት እየተደረገ ይገኛል፡፡

አገዛዙ ሰማያዊን ለማዳከም በተለያዩ አካባቢዎች እየታደኑ የሚታሰሩት የፓርቲ አመራሮቻችንም በተመሳሳይ ሁኔታ ህግ ተነፍጓቸው በእስር ቤት ይገኛሉ፡፡ ባህርዳር ላይ ታስረው የሚገኙ የፓርቲያችን 7 አመራሮች የ15 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ፍርድ ቤቱ ቢወስንም እንደተለመደው ካድሬዎች የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ሽረው በእስር ቤት እንዲቆዩ አድርገዋል፡፡ ሽዋሮቢትና ጎንደር ላይም በርካታ የፓርቲያችን አባላትና አመራሮች ለወራት የታሰሩበት ሳይታወቅ ከቆዩ በኋላ ወደ ማዕከላዊ ተዛውረው ቤተሰብ እንዳይጠይቃቸው ተደርገዋል፡፡

ይህ ፓርቲውን የማዳከም የአገዛዙ ህገ ወጥ እርምጃ አሁንም የቀጠለ ሲሆን ከሳምንት በፊት በአርባ ምንጭ የሰማያዊ ፓርቲ አደራጆችን፣ አባላትንና ቤተሰቦቻቸውን በሀሰተኛ ክስ እስከማሰር ደርሰዋል፡፡ ከታሳሪዎች መካከል የጋሞ ጎፋ ዞን አስተባባሪ የሆነው አቶ ሉሉ መሰለና ቤተሰቦቹ ከሌሊቱ 8 ሰዓት ቤታቸው ተበርብሮ ሲታሰሩ፣ በእስር ላይ የሚገኘው የሰማያዊ ፓርቲ የዞኑ አስተባባሪ አቶ በፍቃዱ አበበ የ65 አመት አዛውንት እናቱ እና እህቱም ታስረው፡፡ አብዛኛዎቹ የዜጎች ሰብአዊ መብት ወደሚገፈፍበትና ጭካኔ ወደሚፈፀምበት ማዕከላዊ እስር ቤት ተዛውረዋል፡፡

የፍትህ ስርዓቱ ለአገዛዙ መግዢያ፣ ፍርድ ቤትም በተራ ካድሬ የሚታዘዝ በመሆኑም ከመቼውም ጊዜ በላይ ህግ ከእነ ካባዋ ተቀብራለች፡፡ ለይስሙላ የተቀመጠው ህግ እስረኞች በቤተሰቦቻቸው፣ በህግ አማካሪዎቻቸው፣ በእምነት አባቶቻቸውና በሌሎችም መጠየቅ እንዳለባቸው ዓለም አቀፍ የሆኑትን የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች ጠቃቅሶ ቢያስቀምጥም በእውኑ ግን እነ እስክንድር ነጋ፣ አንዱዓለም አራጌ፣ ተመስገን ደሳለኝ እና አሁንም በእስር ላይ የሚገኙት በርካታ አባላቶቻችንና ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች እንዳይጠየቁ ተከልክለዋል፡፡ ምግብ እንዳይገባላቸው ይደረጋል፡፡ እስር ቤቱ የሚያደርስባቸውን በደል ለፍርድ ቤት በሚያመለክቱበት ጊዜው ጨለማ ቤት ውስጥ እየታሰሩና እየተደበደቡ ነው፡፡

የፓርቲያችን አባላትና ሌሎች ዜጎች በተለያዩ ጊዜያት ያለ መረጃ ታስረው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እንደተያዘ አገዛዙና በስሩ የሚገኙት ሚዲያዎች ከፍርድ ቤቱ በፊት አጥፊዎች ተብለው ተፈርዶባቸዋል፡፡ ያለ መረጃ በመታሰራቸውና በመከሰሳቸው ይኼው ካድሬ የሚያዘው ፍርድ ቤት ነፃ ሲላቸውም ፖሊስ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ጥሶ እስር ቤት ውስጥ እያከረማቸው ይገኛል፡፡ አገዛዙ የሚደርስበትን ጫና በህግ ሥም ለማቃለልና ህግን ለመግዢያነት እንደሚጠቀምም ያለ ምንም መረጃ ታስረው መረጃ ስላልተገኘባቸው ከበርካታ ስቃይ በኋላ የተለቀቁትን ማስታወስ በቂ ነው፡፡ ለአብነት ከአንድ አመት ስድስት ወር በኋላ በስቃይ እስር ቤት የቆዩት የዞን ዘጠኝ አባላት እና አሁንም በፖሊስ ትዕዛዝ እስር ቤት እንዲቆዩ የተደረጉትን እነ የሺዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ አብርሃ ደስታና ዳንኤል ሺበሽ በታፈነው ፍርድ ቤት እንኳ ነፃ መባላቸው ለፀረ ሽብር ህጉና ሌሎች የመግዢያ ህጎችን ያጋለጠና ፍትህ እንደተቀበረች በግልፅ አሳይቷል፡፡

በአጠቃላይ ዜጎችን ያለ መረጃ አፍኖ ማሰር፣ በቀጠሯቸው አለማቅረብ፣ እንዳይጠየቁ እና ምግብና ሌሎች ቁሳቁሶች እንዳይገቡላቸው መከልከል፣ በፍርድ ቤት ነፃ የተባሉ ይግባኝ ቢጠየቅባቸው እንኳ ከእስር ቤት ውጭ ሆነው መከራከር እየተገባቸው ከእስር እንዳይለቀቁ ማድረግና ሌሎችም በህገ መንግስቱና በአዋጆች አገዛዙ የደነገጋቸውን ሳይቀር መጣሱ በኢትዮጵያ ህግ ለፖለቲካው መሳሪያ እንጅ የበላይነት እንደሌለ ከበቂ በላይ ማስረጃ ነው፡፡ አንድ ሀገር እንደ ሀገር ለመቀጠል፣ ዜጎችም ሀገር አለን ብለው ለመኖር ህግ ትልቅ ነገር እንደመሆኑ አገዛዙ ፍትህ ሥርዓቱን ለራሱ በሚመቸውና በሚጠቅመው መንገድ እየዘወረ ኢትዮጵያንና ዜጎቿን ለባሰ አደጋና ስቃይ እየዳረገ እንደሆነ ተገንዝበናል፡፡ ስለሆነም በኢትዮጵያ ህጋዊ ሥርዓት እንዲመሰረትና የህግ የበላይነት እንዲከበር ሰማያዊ ፓርቲ ትግሉን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ ይህን ትግላችንን ከዳር ለማድረስ የሚመለከታቸው የፖለቲካ ኃይሎች፣ የኢትዮጵያ ህዝብና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ከጎናችን እንዲቆም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
ጥቅምት 24/2008 ዓ.ም
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/48013#sthash.zGEsfXeN.dpuf

አርበኞች ግንቦት 7 ለሁለተኛ ጊዜ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሠራዊት አሰመረቀ * ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ንግግር አድርገዋል



dr birhanu
birhanu nega
አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ለሁለተኛ ጊዜ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት አስመረቀ፡፡
አርበኞች ግንቦት 7 በሁለት ድርጅቶች ማለትም በኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር እና በግንቦት 7 ንቅናቄ ውህደት ጥር 2 ቀን 2007 ዓ.ም ከተመሰረተ በኋላ ከትናትና በፊት እሁድ ዕለት ጥቅምት 7 ቀን 2008 ዓም ለሁለተኛ ጊዜ ብዛት ያላቸውን አርበኛ ታጋዮች ለሦስት ወራት አሰልጥኖ አስመርቋል፡፡
እነዚህ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሁለተኛ ዙር ተመራቂ አርበኛ ታጋዮች ለሦስት ተከታታይ ወራት የተሰጣቸውን የፖለቲካ፣ የወታደራዊ እና ሌሎች ተያያዥ የሆኑ የመረጃና ደህንነት ትምህርቶችን በሚገባ ወስደው በሁሉም መስክ አመርቂ ውጤት በማስመዝገብ ነው ሊመረቁ የቻሉት፡፡
እጅግ በጣም ደማቅ በሆነ ስነ-ስርዓት በተከናወነው የምረቃ በዓል ላይ ከተለያዩ ቦታዎች ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች የታደሙ ሲሆን የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር አርበኛ ታጋይ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የድርጅቱ የትምህርትና ስልጠና መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ታጋይ ተስፋሁን ተገኝ ንግግር በማሰማት ለተመራቂ አርበኛ ታጋዮች መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ከውህደቱ ኋላ የመጀመሪያውን ዙር ሰልጣኞች ያስመረቀው ግንቦት 2 ቀን 2007 ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል፡፡
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47561#sthash.byLB3xXt.dpuf

በስዊድን ለአርበኞች ግንቦት ሰባት መርጃ ገንዘብ ተሰበሰበ

by jeri Emeru


አቶ ዘለሌ ፀጋ ስላሴ ዝግጅቱን ሲከፍቱ
አቶ ዘለሌ ፀጋ ስላሴ ዝግጅቱን ሲከፍቱ

ቅዳሜ ኦክቶበር 31 -2015 (ጥቅምት 20 – 2008 ዓ.ም ) በስዊድን ዋና ከተማ በስቶክሆልም ለአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ መርጃ የሚሆን የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ተደረገ። በዝግጅቱ ላይ በርካታ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ተገኝተዋል።በቦታው ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት አቶ አበበ ቦጋለ  የውጪ እንቢተኝነት ሊቀመንበር እና አቶ ቸኮል ጌታነህ የንቅናቄው ከፍተና አመራር ናቸው።
አቶ አበበ ቦጋለ ንግግር ሲያደርጉ
አቶ አበበ ቦጋለ ንግግር ሲያደርጉ

ዝግጅቱ ረፋዱን 14፡00 ሰዓት የተጀመረ ሲሆን አቶ ጌታሁን ማሬ የዝጅቱ አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ  የስዊድን የአርበኞች ግንቦት ሰባት የስራ አስፈጻሚ ሰብሳቢ የሆኑትን አቶ ዘለሌ ፀጋ ሥላሴን ስለዝግጅቱ ገለጻ እንዲያደርጉና ዝግጅቱንም እንዲመሩ  ጋብዘዋል። አቶ ዘለሌ በበኩላቸው የከተማው የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ያለበትን ሁኔታ ገልጸው እንግዶቹንም በማስተዋወቅ አቶ አበበ ቦጋለና አቶ ቸኮል ጌታሁን ንግግር እንዲያደሩ ጋብዘውል።
አቶ ቸኮል ጌታሁን ንግግር ሲያደርጉ
አቶ ቸኮል ጌታሁን ንግግር ሲያደርጉ
አቶ አበበ በአሁኑ ሰዓት አርበኞች ግንቦት ሰባት እየሰራ ስላለው የስራ ክንውን እቅድና አላማ እንዲሁም ደጋፊዎቹና አባላቶቹ እያደረጉ ስላሉት እንቅስቃሴ ማብራሪያ ሰጥተዋል። አቶ ቸኮል ጌታሁን በበኩላቸው በኤርትራ ቆይታቸው ወቅት ስለተመለከቱት የአርበኛው ቆራጥነትና የአላማ ጠንካራነት የገለጹ ሲሆን በአሁን ሰዓት የድሮ ጀግናችን ስም  በመጥራት የምንቀመጥበት ጊዜ ሳይሆን እኛው እነሱን ተክተን በጀግንነት ስማችን ማስጠራት የሚገባን ጊዜ ነው  በማለት ደጋፊውንና አባላትን የሚአበረታታና የሚነሳሳ መል ክት አስተላልፈዋል።
ከሁለቱ አመራሮች ንግግር በኋላ ተሰብሳቢው ሰው ጥያቄ እንዲያቀርብ ተጋብዞ ለቀረቡት ጥያቄዎች መልስ ተሰጥቷል። እንዲሁም ንቅናቄውን በተመለከተ ግልጽ ውይይት ተደርጓል። ከዚህ በመቀጠል « በደል ይረሳል ወይ?» የሚል ግጥም በማራኪና በወለላዬ ከቀረበ በኋላ  የገቢ ማሰባሰቢያ ጨረታ ተደርጓል። ለጨረታ የቀረበው የንቅናቄው ሊቀመንበር የሆኑት የፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ቆራጡ አርበኛ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከሚመሯቸው አርበኞች ጋር ሆነው የሚታዩበት «ላንቺ ነው ኢትዮጵያ » የተባለ ምስል ሲሆን ይሄው ምስል በግልና በቡድን ተጫርቶ ከፍተኛ ፉክክር ከተደረገ በኋላ  በአንድ መቶ አራት ክሮነር( የስዊድን ገንዘብ ) የስዊድን የስደተኞች ማህበር አሸንፎ ምስሉን የግሉ አድርጎታል። ከዚህ ከጨረታ ከተገኘው ገንዘብ ሌላ ሁለት የቃል ኪዳን ቀለበቶች የመግቢያ ገንዘብ ሦስት መቶ ዶላርና ከእጣ የተሰበሰበ ገቢ ተገኝቷል።
የጨረታው አሸናፊዎች
የጨረታው አሸናፊዎች
በወቅቱ በስደተኛ ማህበሩ አባላት ይደረግ የነበረው ተሳትፎ ዝግጅቱን አድምቆት አርፍዷል በጨረታው ጊዜም በማሃል እረፍት በሚደረግበት ወቅት የ/ሪት ሙሉቀን አማረ «ኢትዮጵያዊት ነሽ አትበሉኝ » የሚል ግጥምና  የ/ሮ ውቤ ማሞ እንዲሁም የአቶ መብራቱ ፀሐዩ  ቀስቃሽ ግጥሞች  ቀርበዋል።
የጨረታው አሸናፊዎች በተቀበሉበት ወቅት
የጨረታው አሸናፊዎች በተቀበሉበት ወቅት
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47992#sthash.2DbljgmM.dpuf

måndag 2 november 2015

See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47912#sthash.DVhGjt6k.dpuf

የፓርላማው ድራማ –  ይገረም ዓለሙ





ሙሉ በሙሉ በአብዮታዊ ዴሞክራቶች በመያዙ የተለየ ሀሳብ የማይሰማበት ሙት የሆነውን ፓርላማ ህይወት ያለው ለማስመሰል የተዘጋጀው ድራማ ማክሰኞ ጥቅምት 16/2008 መታየት ጀምሯል፡፡ ይህ የፓርላማ ድራማ  ቤቴሌቭዥን እንደምናያቸው ድራማዎች ሰሞነኛውን ትኩሳት እየተከተለ በየሳምንቱ የሚጻፍና የሚዘጋጅ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ በዚህ የመጀመሪያ ቀን ትዕይንት መሪ ተዋናይ ሆነው የቀረቡት ጠቅላይ ምኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ  ከፓርላማው አባላት መካከል  በተመረጡት ተዋንያን እየተጠየቁ በመመለስ ሲተውኑ ታይተዋል፡፡

ከቀደሙት ጠቅላይ ምኒስትር ጀምሮ ሲነገር እንጂ ሲተገበር የማይታየው ከተቀዋሚዎች ጋር አብሮ የመስራት ጉዳይ ለመጀመሪያው ቀን ድራማ ማድመቂያነት ከተመረጡት ጉዳዮች አንዱ ነበር፡፡ ተባብሮ መስራት ማለት እንደ ተቀዋሚዎች  በመሰረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በመነጋገር ሀገራዊ መግባባት ከመፍጠር የሚጀምር  እንደ ወያኔ ደግሞ እሱ በሚፈልገው ጉዳይ ሲፈልጋቸው ብቻ በመጥራት የሚገለጽ ነው፡፡ እንዲ ሆነናም  በአምስት ዓመቱ ዕቅድ ላይ ለማወያየት  ምርጫ ቦርድ መዝግቦ ለሚያውቃቸው ፓርቲዎች በሙሉ መንግጨሥታቸው ሰነድና ደብዳቤ መላኩን የገለጹት አቶ ኃይለማሪያም ብዙዎቹ በስብሰባው ላይ ሲገኙ ጥቂቶች ውኃ የማይቋጥር ምክንያት በመስጠት አልተገኙም አሉ፡፡ ያልተገኙት ፓርቲዎች ያቀረቡት ምክንያት ውኃ የማይቋጥር ነው ያሉበትን ምክንያትም ሲያረዱ በሕጋዊ መንግድ የተመረጠ መንግሥት ስላልሆነ ከእርሱ ጋር አንነጋርም ማለታቸው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ለመሆኑ ጥሪያችንን ተቀብለው ብዙዎቹ ተገኝተዋል የተባሉት  ፓርቲዎች የትኞቹና እነማን ናቸው፡፡ዝቅ ብለን እናያቸዋለን፡፡

የመሳሪያ ትግል የሚያካሂዱትን ድርጅቶች አስመልክቶም ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ  ለራሱም መሆን ካልቻለው ሻዕቢያ ጋር ሆነው የሚያመጡት ውጤት ስለማይኖር ጊዜያቸውን በከንቱ ባያባክኑ በማለት ምክር ለመስጠት የዳዳቸው አቶ ኃይለማሪያም አንዳንዶቹ እኮ ጭራሽ የሌሉ ናቸው በማለት ኦነግን ኦብነግንና የጋምቤላ ህዝቦች ንቅናቄን ጠቀሱ፡፡ ይቺ ገለጻ የቀረበችው በደራሲውና  አዘጋጁ ስህተት ይሁን ወይንም በርሳቸው የጥናት ጉደለት ባይታወቅም ሁለት መልእክት ታስተላልፋለች፡፡ አንደኛ እነዚህ የተጠቀሱት ድርጅቶች ሰሞኑን ተባብረው ለመስራት የደረሱበት ስምምነት እነ አቶ ኃይለማያም ሰፈር የፈጠረው ነገር መኖሩን እንድንጠረጥር ያሚያደርግ ፣ ሁለተኛ ደግሞ በሰሜን በኩል ድምጻቸው የሚሰማው ድርጅቶች እነዚህ ብቻ አይደሉምና ለሌሎቹ መኖሮና ጠንካራ መሆን በዘወርዋራ እውቅና የሰጠ ነው፡፡

አቶ ኃይለማሪያም የአቶ መለስ ሌጋስ አስቀጣይ እንደመሆናቸው ስለ ድርጅቶቹ የተናገሩት ከርሳቸው የወሰዱትን ነው፡፡ አቶ መለስ ብረት አንስተው መንግሥታቸውን የሚታገሉ ድርጅቶችን አስመልክቶ ሲላቸው አጥፍተናቸዋል የሉም ሲሉ ሌላ ግዜ ደግሞ በግላቸው ብዙ ርቀት ሄደው ከድርጅቶቹ መሪዎች ጋር ለመገናኘትና ለመደራደር እንደጣሩ ሲናገሩ ሰምተናል፡፡ ሌላ ግዜ ደግሞ ወድመዋል ተደምስሰዋል የተባሉት ደርጅቶች በዚህ ቦታ እንዲህ አደረጉ ጥፋት አደረሱ የሚል ዜና ስንሰማ ኖረናል፡፡ የሉም በተባሉ ድርጅቶች ስምም ዜጎች እየተወነጀሉ ታስረዋል እየታሰሩም ነው፡፡ አቶ መለስ አይደለም የሀገር ውስጥ ተፋላሚዎችን ሶማሌ ተሻግረው አልሻባብን ድምጥማጡን አጥፍተነዋል ብለውንም ነበር፡፡

አቶ ኃይለማሪያም ባያስታውሱም እኛ አንረሳውም፡፡ አቶ መለስ ከርሳቸው ፍላጎት ውጪ ስንዝር መሄድ የማይችለውን ፓርላማ አስፍቅደው(ነግረው)  እንዲህ አስታዋሽ አጥቶ የቀረውን ሰራዊት  ሶማሊያ በላኩበት ወቅት  የገጠማቸውን ተቃውሞ ዝም ለማሰኘት  ሰራዊታችን አልሻባብን ደምስሶ አሁን የቀረው ቃርሚያ ብቻ ነው፣ ያንን አጠናቆ በቅርብ ቀን ይመለሳል ብለውን ነበር፡፡ ነገር ግን ይኸው እስካሁን አልሻባብም አልጠፋ ሰራዊቱም አልተመለሰ፡፡ እንደውም በተቃራኒው ወንድሞቻችን የአልሻባብ ጥቃት ሰለባ እየሆኑ ነው፡፡  አቶ ኃለማሪያም እኔም አንደ መለስ ብለው በንቀት ስሜት የሉም ጠፍተዋል ስላሉዋቸው ድርጅቶች መረጃ ስለሌለኝ የምለው አይኖርም፤ የላችሁም የተባላችሁ መኖራችሁን አሳይዋቸውና አቶ ኃይለማሪም በዚህ አፋቸው ምን እንደሚሉ ለመስማት አብቁን የሚለው ግን መልእክቴ ነው፡፡

አቶ መለስ የሻዕቢያና ወያኔ ጸብና ፍቅር ለወላይታው ምኑ ነው ብለው ለአቶ ኃይለማሪያም አለነገሯቸው እንደሁ እንጂ ወያኔን አዲስ አበባ ያደረሰው ለራሱም የማይሆን ያሉት ሻዕቢያ ነው፡፡ ይህም  ብቻ  አይደለም ሌላው ኢትዮጵያዊ (የወያኔ ታጋይ ጭምር ) የማይታመን ሆኖ እስከ ተጣሉበት ግዜ ድረስ ቤተ መንግሥቱ ይጠበቅ የነበረው በሻዕቢያ ሰራዊት እንደነበረ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ስለሆነም አቶ ኃይለማሪያም ወያኔዎች ስለ ሻዕቢያ ዛሬ የሚሉትን ብቻ እየተቀበሉ መናገር ሳይሆን ትናንት ምን ይሉ ምንስ ያደርጉ እንደነበር የተጻፈ አንብበው የነበረ ጠይቀው ቢናገሩ ቢያንስ ጠቅላይ ምኒስትር ለሚለው ማዕረጋቸው( ይስሙላም ቢሆን) የሚመጥን ይሆናል፡፡

ከላይ እንደተገለጸው አቶ ኃይለማሪያም ስለ አብሮ መስራት ሲናገሩ ምርጫ ቦርድ የመዘገባቸውን ፓርቲዎች በሙሉ ጠርተን አብዛኛዎቹ ተገኝተዋል ነው ያሉት፡፡ አብዛኛው የሚለው የጥቅል መጠሪያ  ለወያኔም ለፓርቲዎቹም ለምርጫ ቦርድም እያገለገለ ነው፡፡ እነዚህ ፓርቲዎች በቁጥር ሲገለጹ እንጂ በስም ሲጠሩ አይሰማም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ምርጫ ቦርድ መዝገብ ላይ ሰፍረው የሚገኙት አንዳንዶቹ የሌሉ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ  ምርጫ ሲመጣ ብቻ ብቅ የሚሉና ለምርጫ የሚሰጣቸውን ገንዘብ ተቀብለው የአጃቢነት ሚናቸውን ተወጥተው ለአራት ዓመት የሚጠፉ ናቸው፡፡ ጥቂቶቹም ፓርቲ ለመባል የሚያበቃ ቁመና የሌላቸው አቶ በረከት የፓርቲዎቹ ጥቅማቸው አልታይ ብሉአቸው ይሁን ስሜት ገፋፍቶአቸው ወይንም እውነት ተናንቆአቸው ባይታወቅም በመጽሀፋቸው የቤተሰብ ፓርቲ ሲሉ  የገለጹዋቸው ናቸው ፡፡  በርግጥ ለመናገር አንዳንዶቹ ሊቀመንበር ተብሎ ከሚጠራው ሰው ቀጥሎ የሚጠራ ሶስትና አራት ሰው የሌላቸው በመሆኑ የቤተሰብ ፓርቲ የሚለውንም አያሟሉም፡፡ ብዙዎቹ ከተባሉት ከእነዚህ ስመ ፓርቲዎች ውስጥ  ብዙዎቹን እንኳን ህብረተሰቡ ምርጫ ቦርድም አያውቃቸው፡፡ ድረ ገጹን ብትጎበኙ ቦርዱ ስለማያውቃቸው የተመዘገቡበትን ቀን መሙላት አቅቶት  ቦታው ክፍት ሆኖ ታገኙታላችሁ፡፡ ፤ብቻ ብዙዎች እየተባሉ ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ይውላሉ፡፡እነዚህን በስም እየጠቀሱ መሪ የሚባሉትን ሰዎች ምንነትና ማንነት እያሳዩ መግለጽ የሚቻል ቢሆንም የሚፈይደው ነገር የለም፡፡ የምርጫ ቦርድን ድረ ገጽ ከጎበኙ  ሌላም ነገር ይታዘባሉ፣ ምርጫ የማስፈጸም ብቃት አለው ተብሎ ምስጋና የተዥጎደጎደለት ይህ ተቋም ድረ- ገጹን ወቅታዊ ማድረግ ተስኖት ከአስር ዓመት በፊት የነበረ መረጃ ነው የሚያገኙት፡፡

ፓርቲ ማለት በምርጫ ቦርድ ተመዝግቦ የህጋዊነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የተሰጠው ነው ካልተባለ በስተቀር  ብዙዎች የሚባሉት ከወያኔ ዳረጎት እየተቀበሉ፤ በምርጫ ቦርድ መልካም ፈቃድ ፓርቲ እየተባሉ፤ በአዳማቂነትና በአጃቢነት  የሚያገለግሉ፣ እንኳን አባል የተሟላ አመራር የሌላቸው ናቸውና ፓርቲ ሊባሉ የሚበቁ አይደሉም፡፡ መሪ ለሚባሉት ሰዎች ግን የእለት እንጀራም የሕይወት መንገድም ሆኖ እየጠቀማቸው ነው፡፡ በአንጻሩ ብዙም ባይሆን ለወያኔ ዕድሜ መርዘምም እየረዱ ነው፡፡ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግን ኖሩም አልኖሩ “ተለበሰ ቀረ የደበሎ ቅዳጅ ”እንደሚባለው ናቸውና ምንም ፋይዳ የላቸውም፡፡ እንደውም የማይቻል ሆኖ እንጂ አለመኖራቸው ይሻል ነበር፡፡

ሙቱን ፓርላማ ህይወት ያለው ለማስመሰል የተጀመረው ድራማ  ደራሲና አዘጋጁ ሰልችቶአቸው እስካላቆሙት ድረስ በጀመረው መልኩ ወቅታዊ የትኩረት አቅጣጫዎችን እየተከተለ የሚቀጥል ይሆናል፡፡ የእኛም ማየትና መስማት ብሎም ከምናይ ከምንሰማው ተነስተን ብዕር ከወረቀት ማገናኘት እንዲሁ ይቀጥላል፡፡እስካላቆሙት ድረስ ያልኩት አቅጣጫ ለማስቀየሻ እየተባሉ በዚህ መልኩ የሚጀመሩ ጉዳዮች ሲዘልቁ ስለማይታይ ነው፡፡ደግሞስ የማስመሰል ስራ መች ብዙ መንገድ ያስኬዳል፡፡ይህ የፓርላማ ድራማ ቀልቡን የሚስበው ሰው ኖር ይሆን!

-