fredag 30 oktober 2015

- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47777#sthash.EXqT2pP1.dpuf

ሚያ ቤት እነ አብርሃ ደስታና ሃብታሙ አያሌውን ፍርድ ቤት ባለማቅረቡ ዳኞች ውሳኔ ሳይሰጡ ቀሩ







በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
የሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸው በፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ እንዲሰናበቱ የተበየነላቸው የአንድነት፣ የሰማያዊ እና የአረና ፓርቲዎች አመራሮች ላይ አቃቤ ህግ ይግባኝ ጠይቆ ጉዳያቸው በጠቅላይ ፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙት አምስት ተከሳሾች ለጥቅምት 22/2008 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል፡፡

ዛሬ ጥቅምት 17/2008 ዓ.ም የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ቢጠበቅም ማረሚያ ቤት ሳያቀርባቸው በሌሉበት ቀጠሮ የተሰጣቸው የፓርቲዎች አመራሮቹ ሀብታሙ አያሌው፣ የሺዋስ አሰፋ፣ አብርሃ ደስታ፣ ዳንኤል ሺበሽ እና አብሯቸው ይግባኝ የተጠየቀበት አብርሃም ሰለሞን ናቸው፡፡

የቂሊንጦ እና የቃሊቲ ማረሚያ ቤቶች እነ ሀብታሙን ፍርድ ቤት ያላቀረቡበትን ምክንያት ፍርድ ቤቱ ሲጠይቅ፣ ‹‹ቃሊቲ በፕላዝማ ይታያል ስለተባለ አላመጣናቸውም፤ ከአይ.ሲ.ቲ ጋር ተነጋግረው ነው ያስቀሯቸው›› የሚል መልስ ተሰጥቷል፡፡ ማረሚያ ቤቱ እነ ሀብታሙን ብቻ ሳይሆን በሌላ መዝገብ በተለያዩ ወንጀሎች ስር የተጠቀሱ ተከሳሾችንም አለማቅረቡ ታውቋል፡፡

ፍርድ ቤቱ በበኩሉ የቃሊቲ ማረሚያ ቤትን መልስ ካደመጠ በኋላ፣ ‹‹ይሄ ቪዲዮ ኮንፈረንስ የሚባል ነገር የሚሆን አይደለም፤ አቅርቧቸው ብለን አዝዘን ነበር፤ እኛ ነን የምናዝዛችሁ ወይስ ማን ነው? አሁንም ቀጣይ ቀጠሮ ላይ አቅርቧቸው›› ሲል በእነ ሀብታሙ መዝገብም በሌሎች መዝገቦችም ላይ ዛሬ ላልቀረቡ ተከሳሾች ተመሳሳይ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ በመሆኑም እነ ሀብታሙ አያሌው ሰኞ ጥቅምት 22/2008 ዓ.ም የተጠየቀባቸው ይግባኝ ያስቀርባል ወይስ አያስቀርብም የሚለውን ብይን ቀርበው ለመስማት ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል፡፡

Related Posts:በእነ ሀብታሙ አያሌው ላይ ተረኛ…

- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47777#sthash.EXqT2pP1.dpuf


torsdag 29 oktober 2015

5 ብሔር ተኮር ነፃ አውጪ ግምባሮች በጋራ የነፃነት እና የዴሞክራሲ ንቅናቄ መሠረቱ


(ዘ-ሐበሻ) በኦስሎ ኖርዌይ ከኦክቶበር 22 እስከ ኦክቶበር 23, 2015 ዓ.ም በተደረገ የጋራ ጉባኤ 5 የኢትዮጵያ የብሄር ድርጅቶች በጋራ ለመታገል አዲስ ንቅናቄ መመስረታቸውን ለዘ-ሐበሻ በላኩት መግለጫ አስታወቁ::
olf ONLF
ጥምረቱን የመሰረቱት የቤኒሻንጉል ነፃ አውጪ ንቅናቄ; የጋምቤላ ነፃ አውጪ ንቅናቄ; የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግምባር; የኦሮሞ ነፃነት ግምባርና የሲዳማ ብሔራዊ ነፃነት ግምባር ሲሆኑ የኢትዮጵያ ያለውን ስርዓት በጋራ ጥለው የሁሉንም ብሄሮች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት የሚያከብርና የአንድን ቡድን የበላይነት እንዲያበቃ የሚያደርግ ስርዓት ለመፍጠር እንደሚታገሉ በመስራች ጉባኤያቸው መጨረሻ ላይ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል::
ሃገሪቱን ወደ ተሻለ የፖለቲካ ሽግግር ቀርጸው ለመንቀሳቀስ የተሰማሙት እነዚሁ 5 ድርጅቶች የአዲሱ ጥምረታቸው መጠሪያ የሕዝቦች ጥምረት ለነፃነትና ለዴሞክራሲ (Peoples Alliance for Freedom and Democracy (PAFD) ተብሎ ተሰይሟል::
አርበኞች ግንቦት በቅርቡ ከአማራው ንቅናቋ; ከአፋር ንቅናቄና ከትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ጋር በጋራ ለመታገል ጥምረት መፍጠሩ ይታወሳል:: ትናንት በኖርዌይ ጥምረታቸውን ያወጁት የቤኒሻንጉል ነፃ አውጪ ንቅናቄ; የጋምቤላ ነፃ አውጪ ንቅናቄ; የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግምባር; የኦሮሞ ነፃነት ግምባርና የሲዳማ ብሔራዊ ነፃነት ግምባር ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር ወደፊት ስለሚፈጥሩት የጋራ ጥምረት ወይም ግንኙነት ይኑራቸው አይኑራቸው የተገለጸ ነገር ባይኖርም በቅርቡ ወደ ሚኒሶታ የመጡት የንቅናቄው የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ነአምን ዘለቀ “ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር እንዳለች እስካመኑ ድረስ ከሁሉም ጋር በጋራ ለመስራት እንችላለን::” ማለታቸውን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም::
ONLF and OLF

የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል፤ ጠ/ሚ/ር ኃይለማሪያም ደሳለኝና በኢትዮጵያ የእንግሊዝ ኤምባሲ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ያሉበትን ቦታ እንዲያሳውቁ ሊጠየቁ ነው


Share0  848  0 
 Share0
  • 848
     
    Share
Andargachew Tsige
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
በእነ ዘመነ ካሴ የክስ መዝገብ ከ2ኛ -5ኛ መዝገብ ለተከሰሱት አቶ አሸናፊ አካሉ (2ኛ ተከሳሽ)፣ አቶ ደናሁን ቤዛ (3ኛ ተከሳሽ)፣ አቶ ምንዳዬ ጥላሁን (4ኛ ተከሳሽ) እና አቶ አንሙት የኔዋስ (5ኛ ተከሳሽ) በመከላከያ ምስክርነት ተጠቅሰው በነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጉዳይ የልደታ ፍርድ ቤት 19ኛው ወንጀል ችሎት ለሶስት አካላት ትዕዛዝ እንዲሰጥ ተጠየቀ፡፡ የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ጥቅምት 12/2008 ዓ.ም አቶ አንዳርጋቸው እሱ ጋር እንደሌሉ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛው ወንጀል ችሎት በላከው ደብዳቤ መግለፁ ይታወሳል፡፡

ከ6ኛ-9ኛ ያሉት ተከሳሾች ማረሚያ ቤቱ በፈጠረው ችግር የአቶ አንዳርጋቸውን ምስክርነት ለመስማት የፍርድ ሂደታቸው እየተጓተተባቸው በመሆኑ የአቶ አንዳርጋቸው ምስክርነት ቀርቶ ብይን እንዲሰጥላቸው ሲጠይቁ 4ኛ ተከሳሽ አቶ ምንዳዬ ጥላሁን ‹‹ከአንዳርጋቸው ጋር ተገናኝተህ መመሪያ ተቀብለሃል ስለተባልኩ አቶ አንዳርጋቸው መጥቶ መመስከር አለበት›› ሲል አሁንም አቶ አንዳርጋቸው እንዲቀርቡለት ጥያቄውን አቅርቦ ነበር፡፡ ከአቶ ምንዳዬ ጥላሁን በተጨማሪ 3ኛ ተከሳሽ አቶ ደናሁን ቤዛም አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲመሰክሩለት በመፈለጉ፤ እና ፍርድ ቤቱም አቶ አንዳርጋቸው ይገኙበታል ተብሎ ለታሰበው ተቋም ትዕዛዝ ለመስጠት እንዲመቸው ተከሳሾቹ እንዲጠቁሙት በገለፀው መሰረት ተከሳሾቹ ፍርድ ቤቱ ለሶስት ተቋማት ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው በደብዳቤ ጠይቀዋል፡፡
negere
ሁለቱ ተከሳሾች ጥቅምት 15/2008 ዓ.ም ለፌደራል ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት በፃፉት ደብዳቤ የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን መያዙን በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንክ ኮርፖሬት መግለጫ መስጠቱን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ መስከረም ወር 2007 ዓ.ም የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌን መያዝ፣ የእድሜ ልክና የሞት ፍርደኛ መሆናቸውን በመግለፅ የኢትዮጵያ መንግስት ፍርዱን ተፈፃሚ እንደሚያደርግ መግለፃቸውን አስታውሰዋል፡፡ በተጨማሪም በኢትዮጵያ የእንግሊዝ ኤምባሲ አቶ አንዳርጋቸው ዜግነታቸው እንግሊዛዊ የሆሉትን አቶ አንዳጋቸው ጉዳይ ላይ ክትትል እንደሚያደርግ በደብዳቤው አስታወስዋል፡፡

በመሆኑም ከእነዚህ ሶስት አካላት በላይ አንዳርጋቸው ፅጌ ስላሉበት ቦታ የሚያውቅ ስለሌለ ለሶስቱም አካላት አቶ አንዳርጋቸው የት እንዳሉ እንዲገልፁና አቶ አንዳርጋቸውም ምስክር እንዲሆኑላቸው ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡

10 የፌ. ፖሊስ አባላት ኮንሶና ቦረና መገንጠያ ድልድይ ላይ ከነመኪናቸው ተደመሰሱ ሲል አርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ ዘገበ


Share1  446  3 
 Share1
  • 446
     
    Share
የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ራድዮ በሰበር ዜናው እንደዘገበው በላንድ ክሩዘር መኪና ተሳፍረው ወደ አርባ ምንጭ ከተማ በፍጥነት ያመሩ የነበሩ 10 የፌደራል ፖሊስ አባላት ኮንሶ እና ቦረና መገንጠያ ድልድይ ላይ ከነመኪናቸው ሙሉ በሙሉ ተደመሰሱ፡፡
ginbot 7እንደ ራድዮው ዘገባ በትናንትናው ዕለት አመሻሽ ላይ አስሩ የፌደራል ፖሊሶች መጀመሪያ አንድ አይሱዙ የጭነት መኪና በኃይል በማስገደድ አስቁመው የተሳፈሩ ሲሆን መኪናው መንቀሳቀስ ሲጀምር “የጫንካቸውን ፖሊሶች አራግፍ አለያ ከነንብረትህ አብረህ ትጋያለህ!” የሚል የስልክ ማስጠንቀቂያ መልዕክት ለአሽከርካሪው በመድረሱ አሽከርካሪው መኪናውን አቁሞ ፖሊሶቹን “አልሄድም” ይላቸዋል፡፡ ቀጥሎም ፌደራል ፖሊሶቹ ሾፌሩን ለማንገራገር ሞክረው ትዕዛዛቸውን በቀላሉ ሊቀበል ባለመቻሉ ስልክ ተደዋውለው ሌላ ላንድ ክሩዘር መኪና እንዲመጣላቸው በማድረግ ተሳፍረው ጉዟቸውን ቀጥለው ኮንሶ እና ቦረና መገንጠያ ድልድይ ላይ ሲደርሱ ቅፅበታዊ ጥቃት ተከፍቶባቸው ከነተሳፈሩበት መኪና ሙሉ በሙሉ ተደምስሰዋል ብሏል የአርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ::
ራድዮው ዘገባውን በመቀጠል የአርባ ምንጭ ከተማ ከፍተኛ ቁጥር ባለው የልዩ ኃይል እና የፌደራል ፖሊስ ጦር ተወራ ጓዳ ጎድጓዳዋ ሳይቀር እየታሰሰ ነው ብሏል::
ራድዮው እንደሚልው እየተፋፋመ ያለው የፀረ-ወያኔ ትግል እየተካሄደባቸው ከሚገኙት የደቡብ ኢትዮጵያ ከተሞች አንዷ አርባ ምንጭ መሆኗ እና በህወሓት የደህንነት ተቋም ጥርስ ውስጥ ገብታ አገዛዙ በአዓይነ ቁራኛ እየተከታተላት የምትገኝ መሆኗ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ከሰሞኑ ደግሞ አርበኞች ግንቦት 7 አንድ አይሱዙ ሙሉ የጦር መሳሪያ ወደ ከተማዋ አስገብቷል በሚል የህወሓት ልዩ ኃይሎች፣ ፌደራል ፖሊሶችና ደህንነቶች በየመንደሩ ተሰራጭተው ከፍተኛ አሰሳ እያደረጉ የነዋሪዎችን የዕለት ተዕለት የህይወት እንቅስቃሴና ሰላም በማወክ ላይ ናቸው፡፡
በተያያዘ ዜና ሙሉጌታ አባ፣ ፀጋዬ ገብረ ፃድቅ እና በኃይሉ ሲሳይ የተባሉ የህወሓት ጆሮ ጠቢዎችና የአካባቢው ቆራጭ ፈላጮች ፎቶግራፋቸው በማህበራዊ ሚዲያው መሰራጨቱን ተከትሎ ከትናንት ምሽት ጀምሮ አርባ ምንጭ ከተማ ከከዚህ ቀደሙ በባሰ ሁኔታ በፌደራል ፖሊስ ተጥለቅልቃ እየታመሰች ትገኛለች ሲል ራድዮው ዘግቧል::
ይህን ዜና የሚያስተባብል መረጃ ከመንግስት በኩል እስካሁን የተሰጠ ነገር የለም:: ዘ-ሐበሻ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ያደረገችው ሙከራም አልተሳካም::

måndag 26 oktober 2015

A High Level Ethiopian Delegation Sent to Russia to Muzzle ESAT Fails

Home » News » A High Level Ethiopian Delegation Sent to Russia to Muzzle ESAT Fails


(ESAT News) – In a desperate attempt to silence an independent Ethiopian TV and radio broadcasting service, the Ethiopian government has reportedly sent a high level delegation to Russia. It was found that the primary mission of the delegation was to demand the Russian government to drop from its satellite the broadcasting of news and programming by the Ethiopian Satellite Television and Radio, known popularly as ESAT.Ethiopian Satellite Television and Radio
The Ethiopian delegation, that comprises senior officials from the Ministries of Defense and Foreign Affairs, has unsuccessfully tried to convince the Russian government that broadcasting of news and programming from ESAT were a threat to the peace and security of Ethiopia.
ESAT, which has millions of loyal viewers and listeners in Ethiopia and in the Diaspora, is funded by individual monthly contributions and fundraising events by Ethiopian communities worldwide. But the ethnocentric regime and its cronies falsely allege that ESAT is funded by a political organization bent on destabilizing the country.
The Ethiopian government, one of the top jailers of journalists, as has been documented by the Committee to Protect Journalists (CPJ), Reporters without Borders, Article 19, Human Rights Watch and other press freedom organizations, has gone as far as asking the Russian government to deny ESAT the use of its satellite. The demand, however, has fallen on deaf ears.
Known for muzzling independent press and dissenting views, the regime in Addis Ababa had installed jamming equipment in its embassy in Moscow. Russian authorities found Ethiopian government’s jamming attempt on Russian soil to be against the law of the land. The Russian Satellite company, after doing its due diligence, has also reportedly rejected demands by Ethiopian authorities to stop its business dealings with ESAT. The Ethiopian government has in the past used diplomatic pressures as well as offering huge payments to satellite companies to thwart the broadcasting of alternative news from ESAT.
The Ethiopian government has so far made over 20 attempts in the last five years to jam and stop ESAT’s broadcasting. According to reports by the Washington Post and the Associated Press, the regime in Ethiopia has also used cyber attack and espionage against ESAT management and journalists to obstruct ESAT’s broadcasting.
ESAT, established five years ago, has now become the only independent news outlet for Ethiopians, who would otherwise be under an information blackout. Telephone messages reaching ESAT from its listeners and broadcasted daily indicate the support form Ethiopians at home and abroad for the continuation ESAT as an alternative news broadcasting service. The listeners also vent their indignation against the regime in Addis for using its meager resources and spending millions of dollars on jamming of satellite broadcasting and cyber espionage to muzzle a news media while millions of Ethiopians are in need of food aid after crops wither again this year.

የኢትዮጵያ ምሑራን በዲሞክራሲ ትግል ውስጥ በስፋት አለመሳተፍ በለውጥ ትግሉ ላይ ያሳደረው ተጽእኖ

October 26, 2015

ጃናሞራ – ከስዊዘርላንድ
ወቅቱን በትክክል አላስታውሰውም ብቻ በግምት በፈረንጆቹ አቆጣጠር 2010 አጋማሽ ወይም መጨረሻ አካባቢ ይመስለኛል። በጀርመናዊቷ ከተማ በፍራንክፈርት አንድ ሕዝባዊ ሥብሰባ ይዘጋጃል። የሥብሰባው አዘጋጆች የያኔው የግንቦት 7 ንቅናቄ የጀርመን አስተባባሪዎች ነበሩ። የስብሰባውም አላማ የግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ የጀመረውን የነጻነት ትግል አስመልክቶ ከኢትዮጵያውያን ጋር በጋራ ለመወያየት ሲሆን በስብሰባው ላይ የተጋበዙት እንግዳ የግንቦት 7 ንቅናቄ ዋና ጸሃፊ የነጻነት ታጋዩና ጀግናው አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ነበሩ።
ስብሰባው እጅግ የተሳካና በስብሰባው ላይ የተካፈሉትን ኢትዮጵያውያን ሥሜት ያረካ ፤ በብዙዎች ጭንቅላት ሲመላለሱ የነበሩ ጥያቄዎችን የመለሰ እንደነበረም ትዝ ይለኛል። በተለይ የተወሰኑ የአገዛዙ ደጋፊዎችና ካድሬዎች አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ ያነጣጠሩ አሉባልታዎችንና የስም ማጥፋት ተረት ተረታቸውን ባሰሙበት ወቅት የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ትዕግስት እና በሳል አስተያየቶች መቼም አይረሱኝም። ከሁሉ በላይ ግን ቀልቤን የሳበውና ለዛሬው ጽሁፌ መነሻ እንዲሆነኝ ያነሳሳኝን አቢይ ጉዳይ ግን እንደሚከተለው አቀርበዋለሁ። የእለቱን ሥብሰባ ለማገባደድ በስብሰባው ላይ የተሳተፉ ኢትዮጵያውያን አስተያየት መስጠት እንደጀመሩ አንድ በፍራንክፈርት ነዋሪ የሆኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ካህን ከመቀመጫቸው በመነሳት መስቀላቸውን በቀኝ እጃቸው ይዘው ካማተቡ በኋላ በስብሰባው ላይ የነበርነውን ታዳሚዎች ሁሉ ያስደመመ እና ያስደነቀ ታሪክ እንዲህ በማለት ጀመሩ።
አንድ አባት ለጉብኝት ወደ ሀገረ አሜሪካ ይሄዱና ቤተሰቦቻቸውን እንዲሁም ወዳጆቻቸውን ከጠያየቁ በኋላ ወደ እናት ሐገራቸው ለመመለስ ይዘጋጃሉ።ታድያ ወደ ሐገር ቤት ከመመለሳቸው በፊት በአንዱ ቀን ወደ አንድ የጉብኝት ሥፍራ ይጓዙና ጉብኝታቸውን ይጀምራሉ። ከጥቂት ደቂቃ በኋላም ወደ አንድ በአጸድ የተሞላ የመቃብር ሥፍራ ይደርሳሉ። እኚህ አባት አጸዱን እያቋረጡ በሚሄዱበት ወቅት አይናቸው ወደ አንድ የመቃብር ሥፍራ ያመራል። ሐውልቱን ትኩር ብለው ሲመለከቱት በሐውልቱ ላይ የተጻፈው የሟቹ የህይወት ታሪክ እጅግ ያስገርማቸዋል። ፕሮፌሰር እከሌ በተወለደ በ 8 ዓመቱ አረፈ ይላል ጽሁፉ፤ እኚህ አባት በጣም ይገረሙና እንዴት ነው ነገሩ? እንዴት አንድ ሰው በስምንት አመት እድሜው ፕሮፌሰር ሊሆን ይችላል? እያሉ በውሥጣቸው እያብሰለሰሉ ወደ ሌላኛው መቃብር ሲጠጉ ሐውልቱ ላይ ዶክተር እከሌ በተወለደ በ3 አመቱ አረፈ የሚል ሌላ ጽሁፍ ይመለከታሉ። አይናቸውን ይጠራጠሩና በመሀረባቸው ጠረግ ጠረግ አድርገው እንደገና ቢመለከቱት ጽሁፉ ተመሳሳይ ሆኖ ያገኙታል። በጣም ተገረሙ! ግራ ተጋቡ! እዚህ ሐገር ደግሞ ትምህርቱ እንዴት ነው? ሲሉ ራሳቸውን ይጠይቁና መልሱን ስላላገኙት ሥለ ጉዳዩ ለመጠየቅና ለመረዳት በማሰላሰል ላይ እያሉ ትንሽ እንደተራመዱ አይናቸው ሌላ መቃብር ላይ ያርፋል። ይህኛው ደግሞ ኢንጂነር እከሌ በተወለደ በ5 አመቱ አረፈ ይላል። እጅግ በጣም ግራ የተጋቡት አባት ሥለ ሁኔታው ለመረዳት በአካባቢያቸው ሥለ ጉዳዩ ሊያስረዳቸው የሚችል ሰው እንዳለ በዓይናቸው ይቃኛሉ። በግርምት ከቆሙበት ሥፍራ ከደቂቃዎች በኋላ አንድ በእድሜያቸው ጠና ያሉ አሜሪካዊ አዛውንት ጠጋ ይሉና የምረዳዎት ነገር ይኖር ይሆን? ሲሉ ይጠይቋቸዋል። እኚህ ኢትዮጵያዊ አባትም ደንገጥ ብለው ኧ ኧ አዎ አዎ አንድ ነገር እንዲያስረዱኝ እፈልጋለሁ ይሉና በአመልካች ጣታቸው ወደ መጀመሪያው ሐውልት እየጠቆሙ በሐውልቱ ላይ ያነበቡትን ታሪክ መናገር ይጀምራሉ። እዚህ የመቃብር ሐውልት ላይ ፕሮፌሰር እከሌ በተወለደ በ8 ዓመቱ አረፈ የሚል ጽሁፍ ይነበባል። እንደገና ያኛው ሐውልት ላይ ደግሞ ዶክተር እከሌ በተወለደ በ3 ዓመቱ አረፈ ይላል። ይህኛው ደግሞ ኢንጂነር እከሌ በተወለደ በ5 ዓሙቱ ማረፉን ይገልጻል ። ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? የዚህ ሐገር ሥርአተ ትምህርትሥ እንዴት ነው? አንድ ሰው በስምንት ዓመት እድሜው ፕሮፌሰር በአምስት እና በሶስት አመት እድሜ ደግሞ ዶክተር እና ኢንጂነር ለመሆን የሚቻለው ብለው ይጠይቃሉ። አሜሪካዊው አዛውንትም ሲመልሱ አዩ አባቴ ይህ ሰው በርግጥ ፕሮፌሰር ነው የተፈጥሮ እድሜውም እዚህ ሐውልቱ ላይ እንደሰፈረው አይደለም። የትምህርት ሥርአቱም ቢሆን ከሌላው ዓለም ብዙም የተለየ ሆኖ አይደለም። ነገር ግን ይህ ይህ ፕሮፌሰር በህይወት ሲኖር ለሐገሩና ለወገኑ የሚጠቅም ተግባር ያከናወነው ስምንት ዓመት ብቻ በመሆኑ በተወለደ በስምንት ዓመቱ አረፈ ተብሎ ሊጻፍ ችሏል። ሌሎቹም ያዩዋቸው ዶክተር እና ኢንጂነር በሕይወት ዘመናቸው ለሕዝባቸውና ለሐገራቸው የሚጠቅም እና የሚበጅ ተግባር የፈጸሙት አምስት እና ሶስት አመታት በመሆኑ የመቃብር ሐውልታቸው ላይ ለትውልዱ ጠቃሚ የሆነ ተግባር የፈጸሙበት አመታት ብቻ ተጻፉ ብለው ያስረዷቸዋል። እኚህ ኢትዮጵያዊ አባትም ባዳመጡት ታሪክ እጅግ ተገርመው እና ተደንቀው ማሰላሰል ይጀምራሉ። ራሳቸውንም እኔስ ለሐገሬ እና ለወገኔ የሚጠቅም ምን ተግባር አከናውኜአለሁ ሲሉ ይጠይቃሉ። በርግጥ እኚህ አባት በሕይወት ዘመናቸው እንደ ሃይማኖት አባትነታቸው የሚጠበቅባቸውን አድርገዋል። ነገር ግን እኚህ አባት በተመስጦ ሲያስቡት እሳቸው በሕይወት ዘመናቸው የፈጸሟቸው ተግባራት ሁሉ አንሰው ይታያቸዋል።
ኢትዮጵያዊው አባትም አሜሪካዊውን አዛውንት አመስግነው የመጨረሻ ጥያቄ አነሱ ። እንዲህ ሲሉ!! በእውነት ከነገሩኝ ታሪክ ብዙ ተማርኩ፤ ወደ ውስጤም ለመመልከት ቻልኩ፤ ራሴንም እኔስ ለወገኔ ምን ሰራሁ ሥል ጠየኩት። ካሉ በኋላ ለመሆኑ እኔሥ ስሞት በመቃብሬ ላይ ምን ተብሎ ሊጻፍ ይችላል ? ሲሉ ጥያቄአቸውን ይሰነዝራሉ። አሜሪካዊው አዛውንትም ጥቂት አሰቡና ለመሆኑ በሕይወት ዘመንዎ ለሐገርዎ እና ለወገኖችዎ የሚጠቅም እና የሚበጅ ምን በጎ ነገር አበርክተዋል ሲሉ ይጠይቃሉ?
ኢትዮጵያዊው አባትም ጥቂት ሲያሰላሥሉ ቆዩና እኔሥ ለሀገሬም ሆነ ለሕዝቤ ይሄ ነው የሚባል የረባ ነገር የፈጸምኩ አይመስለኝም ሲሉ መለሱ። አሜሪካዊው አዛውንትም እንግዲያው እንደ መልስዎ ከሆነና ለሐገርዎና ለሕዝብዎ የሚበጅ በጎ ነገር ያላደረጉ ከሆነ የርስዎ መቃብር ላይ እንደተወለደ አረፈ ተብሎ ይጻፋል አሏቸው !!!!! ብለው ታሪኩን ደመደሙት።
እጅግ አስደናቂ እና አስተማሪ ታሪክ ፡ የሰው ልጅ ያለውን እውቀት ሁሉ ለሌላው ሲያካፍል ፤ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ በጎ ተግባራትን ለመፈጸም ሲዳክር እና ሲደክም ፤ ዘመን ተሻጋሪ የሆነ አስተሳሰብ እና ተግባራት ሲኖሩት ከዚህች ከምንኖርባት አለም ቢያልፍ እንኳን በሕይወት ዘመኑ የፈጸማቸው መልካም ተግባራት ሕያው ሆነው ሥሙ ከመቃብር በላይ ከትውልድ ትውልድ ሲዘከር እንደሚኖር ታሪክ ያስተምረናል።
እንግዲህ ለመግቢያ ያህል ይህንን በኔ አመለካከት ታላቅና አስተማሪ ሊሆን የሚችል ምሳሌአዊ ቁም ነገር ካቀረብኩ በዚህ ጽሁፍ ለማስተላለፍ ወደ ተነሳሁበት መሰረተ ሃሳብ ልለፍ፡
በአንድ ሃገር ውስጥ የተረጋጋ ሰላም እና እድገት እንዲመጣ በሐገሪቷ የሚኖሩ ምሁራን እውቀታቸውን እና ልምዳቸውን አስተባብረው ሙያዊ አስተዋጽኦቸውን ለሚኖሩበት ሓገርና ማህበረሰብ በማካፈል፤ በማስተማር ፤በማስተባበርና፤ አብሮ በመስራት እንዲሁም የተለያዩ አቅጣጫዎችን በማሳየትና በማመላከት የዜግነት ድርሻቸውን ሲወጡ እንደሆነ ከተለያዩ ሓገራት ልምድ በመነሳት መናገር ይቻላል።
ከዚህ አንጻር ኢትዮጵያውያን ምሑራን ካለፉት 50 ዓመታት ጀምሮ በሓገራችን በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ለማስፈን በተደረገው ትግል በተለያዩ ጊዜያት ቀላል የማይባል መስዋእትነት ሲከፍሉ መቆየታቸው የአደባባይ ሚስጥር ነው። ምንም እንኳን በኢትዮጵያ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ትግል ላይ የተካፈሉት ኢትዮጵያውያን ምሑራን ከቁጥራቸው አኳያ ሲታይ ኢምንት ቢሆንም በነጻነት ትግሉ ላይ ትተው ያለፉት አሻራ ግን በቀላሉ የሚዘነጋ አይደለም።
የዚህ ጽሁፍ ዋና ዓላማ በዋናነት ኢትዮጵያዊ ምሑራንን የመተቸት ወይም የመውቀስ ሳይሆን በኔ እይታ ለዘመናት የተደረገው የለውጥ ትግል አመርቂ ውጤት አለማምጣት ዋና ዋና ምክንያቶች ሆነው ያገኘኋቸውን ነጥቦች ለማንሳትና ከተቻለ ጽሁፉን በቅንነት በመመልከት ውይይት ለመጫር እንዲረዳ ነው።
የኢትዮጵያ ምሑራን በዲሞክራሲ ትግል ውስጥ በስፋት አለመሳተፍ በለውጥ ትግሉ ላይ ያሳደረው ተጽእኖ
ሓገራችን ኢትዮጵያ የበርካታ ጎልማሳ እና ዕድሜ ጠገብ ምሑራን ባለቤት ናት።በተለያዩ ጥናቶች ላይ እንደተገለጸው በአሁኑ ወቅት እጅግ በርካታ የተማሩ ዜጎች እና ምሁራን ከሚሰደዱባቸው ሓገራት መካከል የመጀመርያውን ደረጃ ይዛ የምትገኘው ሀገራችን ኢትዮጵያ እንደሆነች በተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች ሲገለጽ ሰንብቷል። እነዚህ ቁጥራቸው እጅግ በርካታ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ምሑራን ከትውልድ ሓገራቸው ለመሰደዳቸው ዋነኛው ምክንያት ደግሞ በሐገራችን ኢትዮጵያ ያለው የፖለቲካ ቀውስ መሆኑ አያጠያይቅም።
ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው ቁጥራቸው እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያን ምሑራን በየዘመናቱ በነበሩ አምባገነን ገዢዎች ጭቆና እና ዘረኝነት ተማረው የሚወዷትን ሐገራቸውን ጥለው በመሰደድ በተለያዩ የአውሮፓ እና የሰሜን አሜሪካ ከተሞች የተሳካላቸው በሙያቸው፡ ዕድል ፊቷን ያዞረችባቸው ደግሞ በተለያዩ የስራ መስኮች ላይ ተሰልፈው ኑሮአቸውን በመግፋት ላይ ይገኛሉ።እንግዲህ በተለያዩ ምክንያቶች ከሚወዷት የትውልድ ሐገራቸው ከተሰደዱት ምሑራን መካከል የአምባገነኖችን አገዛዝ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ አሽቀንጥሮ በመጣል በምትኩ ፍትህ የሰፈነባት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመመስረት በሚደረገው ትግል ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት ምሑራን ቁጥር እጅግ አነስተኛ መሆኑ በለውጥ ትግሉ ላይ ያሳደረው ተጽእኖ ቀላል አይደለም።
ይህንን ስል ግን በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ትግል ላይ የግምባር ሥጋ በመሆን በተለያየ የትግል ዘርፍ መስዋእትነት እየከፈሉ ያሉና የዜግነት ግዴታቸውን እየተወጡ ያሉ ኢትዮጵያውያን ምሑራን እንዳሉ በፍጹም አይዘነጋም ።ለነዚህ ወገኖቼም ታላቅ ክብር እና ፍቅርም አለኝ።
ለመሆኑ በርካታ ምሑራን ወደ ፖለቲካው ትግል መድረክ የማይመጡበት ምክንያቶች ምንድናቸው?
ምሳሌ ላንሳ ከ6 ዓመት በፊት ይመስለኛል በሳይበር ታሪክ የመጀመርያ የሆነ ፓናል ዲስከሽን በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታዎች መወያያ መድረክ (ECADF በወቅቱ እንዳሁኑ በርካታ ሚዲያዎች አልነበሩም ) ይዘጋጃል። በዛ ፓናል ዲስከሽን እንዲሳተፉ በርካታ ኢትዮጵያውያን ምሑራን ፤ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች፤ አክቲቪስቶች እና ጋዜጠኞች ተጋብዘው የነበረ ሲሆን የውይይቱ ርዕስም በርካታ የሆኑ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች የሚታገሉለት ዓላማ እና ማኒፌስቶአቸው ሲታይ በአብዛኛው ተመሳሳይ መሆኑና ሁሉም በኢትዮጵያ የዴሞክራሲያዊ ሥርዐት ለመመሥረት የሚታገሉ መሆናቸውን እየገለጹ ነገር ግን የጋራ ጠላታቸውን ለመታገል በህብረት ሲሰሩ አለመታየታቸውን አስመልክቶ እነዚህ የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችን በጋራ ሊያሰራቸው የሚችል ሚኒመም አጀንዳ ምንድነው የሚል ነበር። በዚህ ውይይት ላይ እንዲሳተፉ ከተጠየቁት በርካታ ምሑራን መካከል ጥቂቶቹ ፈቃደኝነታቸውን በመግለጽ በውይይቱ ላይ በመሳተፍ እውቀታቸውን እና ልምዳቸውን በመጠቀም ለውይይቱ ተሳታፊዎች እና ለታዳሚዎቻቸው ይበጃል ያሉትን አስተያየታቸውን ያካፈሉ ሲሆን በርካቶቹ ግን በውይይቱ ላይ ለመሳተፍ ፍቃደኞች አልነበሩም። በውይይቱ ላይ ላለመሳተፍ ያቀርቡ የነበረው ምክንያት ግን እጅግ አሳዛኝ እና አስገራሚ ነበር። ለምሳሌ አንዳንዶቹ ካነሷቸው ምክንያቶች ውስጥ በውይይቱ ቢሳተፉ በገዢው መንግስት ካድሬዎች ጥቃት ሊደርስባቸው እንደሚችል ፤ ወደ ሐገር ቤት ለመሄድ በዝግጅት ላይ በመሆናቸው እንዲህ አይነት ውይይት ላይ መሳተፍ እንደማይችሉ ፤ አንዳንዶቹም ጉዳዩ ፍጹም እንደማይመለከታቸው እና እንደማያሳስባቸው ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ ከውይይቱ በኋላ ሊደርስባቸው ስለሚችል ትችት እና ዘለፋ በነሱ አገላለጽ ስድብ ምክንያት በውይይቱ ላለመሳተፍ እንደወሰኑ ነበር የገለጹት። ሌላው እጅግ የሚያሳዝነው በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የገዘፈ ስም ያላቸው ምሑራን ጭምር ለውይይት ሲጋበዙ የሌሎችን ተጋባዦች ስም በመጠየቅ እሱ ብሎ ምሑር፤ እሷ ብሎ ምሁር ፤ እሱ ካለ አልመጣም፤ እሷ ካለች አልመጣም በማለት ከአንድ እድሜ ጠገብ ምሁር ፖለቲከኛ የማይጠበቅ አሳፋሪ እና አሳዛኝ መልስ በመስጠት በውይይቱ ሳይሳተፉ መቅረታቸውን አስታውሳለሁ። ይህ አይነቱ ችግር አሁንም ድረስ የቀጠለ እና አፋጣኝ መፍትሄ የሚያስፈልገው አቢይ ችግር እንደሆነ የተለያዩ በዘርፉ ላይ የተሰማሩ ጋዜጠኞች ሲናገሩ ይደመጣል።
ከነዚህ ከላይ ከተጠቀሱት ምክንያቶች መካከል በተለይ ትችትን እና ስድብን በመፍራት ወይም በመጥላት ራስን ገለልተኛ በማድረግ ከምንም ነገር ነጻ አድርጎ ለመቀመጥ መሞከር ከአንድ ፊደል ከቆጠረ እና ከፍተኛ እውቀትን ከገበየ ዜጋ የሚጠበቅ አይደለም። ይህ የተያያዝነው የነጻነት ትግል እንዲህ በቀላሉ የማይታይና እጅግ ከባድ የሆነ ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑም መዘንጋት የለበትም። ነጻነትም በነጻ እንዲሁ ሳይደክሙ እና ሳይለፉ የማይገኝ ክቡር እና ውድ ከፈጣሪ የተሰጠን ጸጋ መሆኑን ለአፍታ እንኳን ልንዘነጋው አይገባም። በአንድ ወቅት አንድ ኢትዮጵያዊ ፖለቲከኛ ስለተሳዳቢዎች ተጠይቆ የመለሰውን መልስ ልዋስ * ተሳዳቢ ለመሆን ትምህርት ቤት መሄድ አያስፈልግም ተሳዳቢ ለመሆን የሚያስፈልገው ክራይቴሪያ ባለጌ መሆን ብቻ ነው ነበር ያለው * እናም የባለጌዎችን ስድብ እና ትችት ፈርተን እጅግ ክቡር የሆነውን ነጻነታችንን ለመቀዳጀት ከሚደረግ ትግል መራቅ ከሕሊና ተጠያቂነት አያድንም። በዚህ የነጻነት የሞት ሽረት ትግል ውስጥ ምትክ የማይገኝላትን ሕይወታቸውን ለነጻነታቸው እና ለሐገራቸው ሉአላዊነት ለመሰዋት በበረሃ የተሰለፉ ጀግኖች ወንድሞች እና እህቶች አሉና !! ከጊዜያዊ ከበሬታ ይልቅ ዘላቂ እና ቋሚ የሆነው ነጻነታችን ከምንም ነገር በላይ ቀዳሚ ነውና !!
ሌላው በተለያየ የሙያ ዘርፍ ከፍተኛ እውቀት እና ልምድ ያላቸው ምሑራን በተለያዩ ምክንያቶች በዴሞክራሲያዊ ትግሉ ላይ ባለመሳተፋቸውና ቸልተኝነት በማሳየታቸው የተለያዩ የማህበረሰብ መገናኛ ዘዴዎችን እና የፖለቲካ መድረኩን ሐገራዊ ራዕይ የሌላቸው፤ በስሜት የሚመሩና ካለነሱ ሰው ያለ የማይመስላቸው፤ ለግል ጥቅማቸው የሚዳክሩ የዕውቀት እና የእውነት ድሖች የሆኑ ብልጣብልጦችን በየመድረኩ ላይ እንዲፈነጩበት አድርጓቸዋል። እነዚህ የአስተሳሰብ እና የዕምነት ድሆች ደግሞ በነጻነት ትግሉ ላይ ደንቃራ በመሆን ትግሉን ወደኋላ ለመጎተት ሲፍጨረጨሩ ይስተዋላሉ። እነዚህ ከራሳቸው ጥቅም ውጭ ሌላ ነገር የማይታያቸው ስግብግብ ግለሰቦች ተልኮአቸው ከአንዱ የፖለቲካ ድርጅት ወደ ሌላው በመዝለል ድርጅቶችን ማዳከም ሲሆን በተጨማሪም ኢትዮጵያውያን የሚሰባሰቡባቸውን ኮሚኒቲዎች እና የእምነት ተቋሞችን ሳይቀር በማዳከም እና በማፈራረስ ኢትዮጵያዊው ተስፋ ቆርጦ ቤቱን ዘግቶ እንዲቀመጥ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም።
በአንዳንድ አካባቢዎች በሐገሩ መኖር ተስኖት ሕይወቱን ለማስተካከል የሚሰደደውን ኢትዮጵያዊ ሥደተኛ የድጋፍ ወረቀት እንጽፋለን በሚል ለፍቶ የሚያገኛትን ሳንቲም መዝረፍን፤ በእምነት ተቋማት ውስጥ ሰርጎ በመግባት ከምእመናን የሚሰበሰበውን ሙዳየ ምጽዋት መስበርን ኑሮአቸው አድርገው ተያይዘውታል። በመሆኑም እንደነዚህ አይነቶቹን ደካሞች በቃችሁ ካላልናቸውና ብቃቱና ችሎታው ያላቸውን ዜጎች መተካት ካልቻልን በተለያዩ ተቋማት ውስጥ የተሰገሰጉት ሆድ አደሮችና የግልጥቅም ያሳወራቸው ደካሞች ኮሚኒቲዎቻችንን ማዳከምና ማፈራረስ በእምነት ተቋሞቻችንም ውስጥ ገብተው ሙዳየ ምጽዋት መስበራቸውን አያቆሙም።
ሌላው ሳልጠቅሰው የማላልፈው በአንዳንድ ምሑራን ዘንድ የሚንጸባረቀውን የርሥ በርስ መጠላለፍ እና አለመከባበር እንዲሁም የራስን ድክመት ለመሸፈን የሌሎችን ግድፈት ነቅሶ የማውጣት አባዜ ነው። የተያያዝነው የነጻነት ትግል እጅግ አድካሚና ከፍተኛ መስዋዕትነት የሚጠይቅ መሆኑ እየታወቀ ሁሉም ጠጠሩን በጋራ ጠላቱ ላይ ከመወርወር ይልቅ ትኩረትን ወደ ጎን አዙሮ እርሥ በርስ መናቆር እና እኔን ብቻ ስሙኝ ፖለቲካ የትም ሊያደርሰን እንዳልቻለ ካለፈው ተሞክሮአችን መረዳት ይቻላል። ሁሉም አካባቢውን ቢያጸዳ ከተማችን የጸዳች ትሆናለች የሚል መፈክር ትዝ ይለኛል። አዎ ሁላችንም ትኩረታችንን ወደ ዋናው ጠላታችን በማዞር የድርሻችንን ብንወጣ የምንመኘውን ነጻነት እና ዴሞክራሲያዊ ሥርአት እውን ማድረግ እንችላለን።
አንድ ምሳሌ ላንሳ ከ 5 ዓመት በፊት የተከናወነ ጉዳይ ነው። በወቅቱ በጣም ያስገረመኝ እና ያሳዘነኝ ጉዳይ በመሆኑ ከላይ ለመጥቀስ የሞከርኩትን የመጠላለፍ እና እኔ እበልጥ አተካራ ሊያስረዳልኝ ይችላል በማለት አነሳዋለሁ።
Mr. X በሙያቸው ኢኮኖሚስት የሆኑ ታዋቂ ፖለቲከኛ እና ምሑር ሲሆኑ በነጻነት ትግሉውስጥ ከፊት በመሆን የዜግነት ድርሻቸውን በመወጣት ላይ የሚገኙ ናቸው። Mr. Y እንዲሁ በሙያቸው ኢኮኖሚስት የሆኑና በተለያዩ ድህረ ገጾች ላይ አስተማሪና ጠቃሚ የሆኑ አርቲክሎችን በመጻፍ የበኩላቸውን አስተዋጽዖ የሚያበረክቱ ናቸው።
ታድያ ከዕለታት በአንዱ ቀን በአንድ የአውሮፓ ከተማ ሥለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ጉዳይ ለመወያየት እና ሐገሪቱ ያለችበትን ሁኔታ ለማስረዳት ሥብሰባ ይዘጋጃል። በዚህ ውይይት ላይ ተገኝተው ንግግር እንዲያደርጉ ከላይ የጠቀስኳቸው ሁለት ምሑራን ይጋበዛሉ። የሥብሰባው አዘጋጆች ውይይቱን Mr. X የኢትዮጵያን ፖለቲካ አስመልክቶ ንግግር እንዲያደርጉ ሲነገራቸው በደሥታ ተቀብለው ለውይይቱ ዝግጅታቸውን ይጀምራሉ። Mr. Y ደግሞ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ አስመልክቶ ንግግር እንዲያደርጉ ይነገራቸውና ተስማምተው የስብሰባው ቀን ይጠበቃል። እንዳይደርስ የለም የስብሰባው ቀን በጉጉት እየተጠበቀ ባለበት ወቅት ውይይቱ ሊካሄድ አንድ ቀን ሲቀረው Mr. Y ለስብሰባው አዘጋጆች በውይይቱ ላይ እንደማይገኙ በኢሜል ያሳውቃሉ። የውይይቱ አዘጋጆችም በሁኔታው ተደናግጠው ሥለ ሁኔታው ማብራርያ ይጠይቃሉ Mr. Y ግን ሌላ ቀጠሮ ሥላላቸው መምጣት እንደማይችሉ ይገልጻሉ። የውይይቱ አዘጋጆችም በዛ ሁኔታ ሌላ ሰው ለመጋበዝ በቂ ጊዜ ባለመኖሩ ለ Mr. X የተፈጠረውን ችግር አስረድተው እሳቸው ሁለቱንም አርዕስት እንዲሸፍኑ ይደረግና ውይይቱ በዕለቱ ይከናወናል።
ታድያ እጅግ የሚገርመው እና የሚደንቀው Mr. Y በውይይቱ እንደማይካፈሉ በገለጹበት ወቅት ማለትም ከውይይቱ አንድ ቀን በፊት ለውይይቱ አዘጋጆች ኢሜል በላኩበት ቅጽበት ማለት ነው 15 ገጽ ያለው ጽሁፍ በኢንተርኔት ይበትናሉ። ጽሁፉም የሚያጠነጥነው በውይይቱ ላይ አብረዋቸው እንዲሳተፉ የተጋበዙት Mr. X በአንድ ወቅት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ አስመልክተው የጻፉትን ጽሁፍ የሚያጣጥልና ግድፈት ያለበት መሆኑን የሚገልጽ ነበር። Mr. Y ጽሁፉን ማውጣታቸው መብታቸው ቢሆን እንኳን ጽሁፉን ለማውጣት የመረጡት ቀን ሆን ተብሎ የ Mr. Xን ሙያዊ ብቃት ለማሳነስና በውይይቱ ላይ እንቅፋት ለመፍጠር ሆን ብለው ያደረጉት መሆኑን መገመት ይቻላል። በተጨማሪም Mr. Y በውይይቱ ላይ ተካፍለው ለውይይቱ ተሳታፊዎች እና ውይይቱን በተለያየ መንገድ ለሚያደምጡ ዜጎች ከእውቀታቸው ቢያካፍሉ የተሻለ ይሆን ነበር። እዚህ ላይ Mr. Y ሃሳባቸውን ለምን በጽሁፍ አቀረቡ የሚል አመለካከት የለኝም ነገር ግን የሌሎችን ድክመት በማሳየት አዋቂ ለመምሰል ከመጣር የራሥን ጥንካሬ በተግባር በማሳየት ሌሎችን ለማስተማር መሞከር ብልህነትና አዋቂነት መሆኑን ለማሳየት ነው።
በአጠቃላይ ይሉኝታ ፤ ፍርሐት ፤ቸልተኝነት ፤ራሥ ወዳድነት ፤ጊዜያዊ ከበሬታን ፍለጋ ፤መጠላለፍ ፤እኒ እበልጥ እኒ እበልጥ፤ እኒ ከሌለሁ አፈርሰዋለሁ የሚሉት በሽታ ፤በሕዝብ ትግል ራስን ለማሳደግ መጣር ፤ሥግብግብነት ወዘተርፈ የሚባሉ ጥርቅምቃሚ አመሎች የነጻነት ትግሉን ክፉኛ እየጎዱ መሆናቸው የአደባባይ ሚስጥር ሆኗል።
በነገራችን ላይ በዚህ ጽሁፍ ላይ ከሌላው የማሕበረሰብ አባላት የተሻለ ግንዛቤና እውቀት ስላላቸው አስተያየቴን በምሑራን ላይ አተኮርኩ እንጂ ይህ ችግር በሁሉም ኢትዮጵያዊ በአብዛኛው የሚንጸባረቅ መድሀኒት የሚያሻው የፖለቲካ ኢቦላ ነው:: በተጨማሪም ምሑራኖች በተለያዩ ዘርፎች የሚያነሷቸው የግል ሃሳቦችና ውሳኔዎቻቸው ፈጣን የሕዝብ ድጋፍና መነሳሳትን በመፍጠር በሐገሪቱ አጠቃላይ ፖለቲካ ላይ ጉልሕ ተጽዕኖ ማሳደር የሚችል በመሆኑ የኢትዮጵያ ምሑራንም ሐገራችን ከገባችበት አዘቅት የምትወጣበትን መላ በመዘየድ የመሪ እና የአቅጣጫ አመላካችነት ሚናቸውን በግምባር ቀደምትነት መወጣት ይጠበቅባቸዋል የሚል የጸና እምነት ስላለኝ ነው።
ዛሬ በስደት የምንኖርባቸው የአውሮፓ እና የሰሜን አሜሪካ ሐገራት ከመሬት ተነስተው አሁን ያሉበት ደረጃ ላይ እንዳልደረሱ ግልጽ ነው። እንደሚታወቀው የቀደመው ትውልድ ምሑራን ሕዝብን በማስተባበር ከፍተኛ መስዋእትነት እና ከባድ ዋጋ ከፍለው ለዛሬው ትውልድ መሰረት እንደጣሉ ሁላችንም የምናውቀው ሀቅ ነው። እንግዲህ እኛም ሐገራችን እንደ ሐገር እንድትቀጥል እና ሌሎች የደረሱበት ደረጃ እንድትደርስ የምንፈልግ ከሆነ ሁላችንም ዛሬ ነገ ሳንል አሁኑኑ የድርሻችንን መወጣት ይጠበቅብናል። አለበለዚያ ያቺ የምንመኛት ዘመናዊት ዴሞክራሲያዊት ኤትዮጵያ እንደ መና ከሰማይ አትወርድም። እኛው አምጠን ካልወለድናት።
በመጨረሻም ምንም እንኳን መማር የተፈጥሮን ባህርይ ሙሉ በሙሉ መለወጥ ባይችልም የሰውን ልጅ ባህርይ ለመግራት ያለው አቅም ግን ከፍተኛ መሆኑ አያጠያይቅም። መማር አይነ ልቦናን ይከፍታል፤ ክፉና ደጉን ለመለየት ያግዛል፤ ተፈጥሮን ለመመርመር ይረዳል ። አይነ ልቦና ሲከፈት ደግሞ የችግሮቹ ሁሉ መንስኤዎች ፍንትው ብለው ይታያሉ ። ያኔ መፍትሔውም በእጃችን እንዳለ መረዳት ከባድ አይሆንም።
እንግዲህ ከላይ በጽሁፉ መግቢያ ላይ እንደተቀመጠው ሁላችንም ለሀገራችንና ለወገናችን ሊጠቅም የሚችል በጎ ነገር መስራታችንን ራሳችንን እንጠይቅ። አንድ ሰው በዚህ ምድር ላይ ይሄን ያህል ጊዜ ኖሮ አለፈ የሚባለው በህይወት ዘመኑ ለሐገር እና ለወገን የሚበጅ እና የሚጠቅም መልካም ነገር አበርክቶ የድርሻውን ተወጥቶ ሲያልፍ ብቻ ነው። መልካም የሰራ ሥራው ለዘላለም ሕያው ሆኖ ይኖራልና !! ሥም ከመቃብር በላይ ይኖራል ይባል የለ !!
ጃናሞራ
janamoraeth@gmail.com

የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንደሌሉ ገለፀ (ነገረ ኢትዮጵያ)

October 23, 2015
• ‹‹የስርዓቱን ሽፍትነት ያመላክታል›› 3ኛ ተከሳሽ አቶ ደናሁን ቤዛ
• ‹‹የሚቀርብልን ምግብ ለእንሰሳትም መቅረብ የማይገባው ነው›› 2ኛ ተከሳሽ አቶ አሸናፊ አካሉ
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
በእነ ዘመነ ካሴ የክስ መዝገብ ከ2ኛ -5ኛ መዝገብ ለተከሰሱት አቶ አሸናፊ አካሉ (2ኛ ተከሳሽ)፣ አቶ ደናሁን ቤዛ (3ኛ ተከሳሽ)፣ አቶ ምንዳዬ ጥላሁን (4ኛ ተከሳሽ) እና አቶ አንሙት የኔዋስ (5ኛ ተከሳሽ) በመከላከያ ምስክርነት የተጠቀሱት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንደሌሉ ማረሚያ ቤቱ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛው ወንጀል ችሎት በላከው ደብዳቤ ገልፆአል፡፡ 19ኛ ወንጀል ችሎት ሀምሌ 29/2007 ዓ.ም የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አቶ አንዳርጋቸውን ለምን እንዳላቀረበ እንዲያብራራ፣ እንዲሁም ለምስክርነት እንዲያቀርብ ለዛሬ ለጥቅምት 12/2008 ዓ.ም ለአራተኛ ጊዜ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበር ቢሆንም ማረሚያ ቤቱ አቶ አንዳርጋቸው ቃሊቲ እንደሌሉ በደብዳቤ አሳውቋል፡፡Ato Andargachew Tsige, Ginbot 7
ተከሳሾቹ ማረሚያ ቤቱ ሲያጉላላቸው ቆይቶ አሁን የለም ማለቱ ትክክል እንዳልሆነ የገለፁ ሲሆን 2ኛ ተከሳሽ አቶ አሸናፊ አካሉ ማረሚያ ቤቱ ምላሽ የሰጠው በአራተኛው ትዕዛዝ መሆኑን ጠቅሶ የፍርድ ሂደታቸውን ከሚገባው በላይ እያጓተተ እንደሆነ ለፍርድ ቤቱ ገልፆአል፡፡ ‹‹መከላከል ከጀመርን አንድ አመት ከስድስት ወር ሆነ፡፡ በግዞት ነው ያለነው፡፡ የሚቀርብልን ምግብ ለእንሰሳትም መቅረብ የማይገባው ነው›› ያለው አቶ አሸናፊ የማረሚያ ቤቱን ምላሽ ‹‹ፌዝ ነው›› ብሎታል፡፡
3ኛ ተከሳሽ አቶ ደናሁን ቤዛ በበኩሉ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በመከላከያ ምስክርነት ሲጠቅሱ አቃቤ ህግ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ የሞትና የእድሜ ልክ ፍርደኛ እንደሆኑ በመጠቆም ተቃውሞ አሰምቶ እንደነበር፣ የእድሜ ልክና የሞት ፍርደኛ ቃሊቲ እንደሚታሰር ገልፆ ማረሚያ ቤቱ አቶ አንዳርጋቸው እንደሌሉ መግለፁ ‹‹የስርዓቱን ሽፍትነት ያመላክታል›› ብሏል፡፡ ‹‹የእድሜ ልክ ወይንም የሞት ፍርደኛ የት ነው የሚታሰረው?›› ሲልም ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡
3ቱ ተከሳሾች የፀረ ሽብር ግብረ ኃይሉና ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ አንዳርጋቸውን እንደያዙ በቴሊቪዥን መግለፃቸውን አስታውሰው አሁንም ለሁለቱ አካላት ደብዳቤ እንደሚፅፉ ለፍርድ ቤቱ አሳውቀው የነበር ቢሆንም ከ6ኛ-9ኛ ያሉት ተከሳሾች ማረሚያ ቤቱ በፈጠረው ችግር የአቶ አንዳርጋቸውን ምስክርነት ለመስማት የፍርድ ሂደታቸው እየተጓተተባቸው በመሆኑ የአቶ አንዳርጋቸው ምስክርነት ቀርቶ ብይን እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡
ሆኖም ግን 4ኛ ተከሳሽ አቶ ምንዳዬ ጥላሁን ‹‹ከአንዳርጋቸው ጋር ተገናኝተህ መመሪያ ተቀብለሃል ስለተባልኩ አቶ አንዳርጋቸው መጥቶ መመስከር አለበት›› ሲል አሁንም አቶ አንዳርጋቸው እንዲቀርቡለት ጥያቄውን አቅርቧል፡፡ ፍርድ ቤቱም 4ኛ ተከሳሽ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲቀርቡለት የሚያቀርበውን አቤቱታ ተመልክቶ ይገኙበታል ተብሎ ለታሰበው ተቋም ትዕዛዝ ለመስጠት ለጥቅምት 23/2008 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡